Your cart is currently empty!
ሙለተ ሃዩ የትምህርት ኢንስቲቲዩት ሃላፊነቱ የተወስነ የግል ማህበር በትምህርት ላይ የሚሰራ ሃላፊነቱ የተወስነ የግል ማህበር ሲሆን እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር የ 2018 ዓ.ም ሂሳብ ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል
Reporter(Aug 20, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
ሙለተ ሃዩ የትምህርት ኢንስቲቲዩት ሃላፊነቱ የተወስነ የግል ማህበር በትምህርት ላይ የሚሰራ ሃላፊነቱ የተወስነ የግል ማህበር ሲሆን እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር የ 2018 ዓ.ም ሂሳብ ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል።
ስለሆነም ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች ሥራውን ለማከናወን የሚጠይቁትን የገንዘብ መጠንና ሥራውን ለማጠናቀቅ የሚፈጅባቸውን ጊዜ በመጥቀስ፣ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሰባት ተከታታይ የሥራ ቀናት ከታች በተገለጸው አድራሻ መሠረት በፖስታ አሽገው በማስገባት መወዳደር ይችላሉ።
የኦዲት ድርጅቶቹ የሚከተሉትን መመዘኛዎች ማሟላት አለባቸው፡–
ሀ. ኦዲተሩ የሙያ ማረጋገጫ ያለው መሆኑ፣
ለ. የንግድ ፈቃድ ያለው መሆኑ፣
ሐ. የዘመኑን ግብር ስለመክፈሉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆኑ፣
መ. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው መሆኑ፣
ሠ. ከፌዴራል ወይም ከክልል ኦዲተር መሥሪያ ቤት ለበጀት ዓመቱ የታደሰ ፈቃድ ያለው መሆኑ።
አድራሻ፡– ሸገር ከተማ ቡራዩ ክ/ከተማ ከቡራዩ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ፊት ለፊት
ለበለጠ መረጃ፡– በስልክ ቁጥር 0901210000 /የቢሮ/
0961604814/ /0900042360 ሞባይል/ ይቻላል።