Your cart is currently empty!
በቂርቆስ ክ/ከ/አስ/በዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ኮምፒውተሮች እና ጀነሬተሮች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 20, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2018
በቂርቆስ ክ/ከ/አስ/በዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት የግዥ ቡድን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ለከተማ አስተዳደሩ አገልግሎት የሚውሉ ኮምፒውተሮች እና ጀነሬተሮች ግዥዎችን ከዚህ በታች የተጠቀሱ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1 የኮምፒውተር ግዥ
- ሎት 2 የጀነሬተር ግዥ
በመሆኑም ተጫራቾች፡–
1. በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ የስራ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር/tin no/የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
2. የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
3. ለሚወዳደሩባቸው የሎት አይነቶች የጨረታ ማስከበሪያ ከጨረታ ሰነዱ ላይ የተጠቀሰውን በሲፒኦ ብቻ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
4. የጨረታው ሰነድ አቀራረብ 1 ቴክኒካል ሰነድ ኦሪጅናል 1 ቴክኒካል ሰነድ ኮፒ 1 ፋይናንሽያል ሰነድ ኦሪጅናል እና የፋይናንሽያል ኮፒ ለየብቻ እንዲሁም 1 ሲፒኦ ለብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለበት፡፡
5. የጨረታ ሰነዱን እስጢፋኖስ ላይ በሚገኘው የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አዲሱ ህንፃ 9ኛ ፎቅ የዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
6, ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንድ ቀን ብሎ በመቁጠር 11ኛው ቀን ላይ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋ ሲሆን በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ጨረታው ይከፈታል።
7. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ላይ እንደ ማሳሰቢያ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡– እስጢፋኖስ ከሚገኘው ከማሪዎት ሆቴል ፊት ለፌት የቂርቆስ ክ/ከ/አሰ/ አዲሱ ህንፃ 9ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር፡– 011 554 8264 / 011 869-4366
በአዲስ አበባ የቂርቆስ ክ/ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት