Your cart is currently empty!
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የጅማ ገነቲ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎችን፣ አላቂ የቢሮ እቃዎችን፣ ቋሚ እቃዎችን፣ የህንፃ መሳሪያዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችንና የደንብ ልብሶችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 21, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የጅማ ገነቲ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎችን፤ አላቂ የቢሮ እቃዎችን፤ ቋሚ እቃዎችን፤ የህንፃ መሳሪያዎችን፤ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ና የደምብ ልብሶችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ተጫራቾች ፡–
1. በዚህ ስራ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
2. ከገ/ጽ/ቤት የአቅራብነት የምስክር ወረቀት እና ተጫማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆናቸውን የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. የጨረታውን ሰነድ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በጅማ ገነቲ ወረዳ ገቢዎች ባለስልጣን ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር.2 የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ) ከፍለው ጨረታው ከወጣበት ቀን ነሐሴ 15/12/2017 ዓ.ም ተከታታይ 15 የስራ ቀናት መካከል በየቀኑ ከ2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የተጫረቱበትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ 30,000/ ሰላሳ ሺ ህ ብር/ በCBE በባንክ በተረጋገጠ CPO ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር በማያያዝ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ኦሪጅናልና ኮፕ ሰነድ ማቅረብ አለባቸው።
5. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች VAT ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ሰነድ ማቅረብ አለባቸው።
6. የሚያቀርቡትን ̧ የዋጋ ሰነድ ጨረታ ከወጣበት ቀን 15/12/ 2017 ዓ.ም እስከ መስከረም 5/1/2018 ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ በሆሮ ድሩ ወለጋ ዞን በጅማ ገነቲ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 11 ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. ጨረታው መስከረም 5/1/2018 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ 4፡30 በጅማ ገነቲ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 11 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
8. ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በራሳቸው ወጪ እቃውን የሚያቀርቡት በጅማ ገነቲ ወረዳ ሐረቶ ከተማ ገ/ጽ/ቤት ድረስ ይሆናል።
9. በሰነዱ ላይ የተጠቀሰው የእቃው ብዛት (Quantity) 20% ለመቀነስም ሆነ ለመጨመር መስሪያቤቱ ሙሉ መብት አለው።
10. መስሪያቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0910 420 92 , 0917 854 572 , 0920 415 163
በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የጅማ ገነቲ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት