Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የፕሮጀክቶች ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት ለካራ ቆሬ ዕቃ ግምጃ ቤት የአጥር ግንባታ የእጅ ስራ በዘርፉ ከተሰማሩ ደረጃ 8 እና ከዛ በላይ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 22, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር EEU/PPM/05/2018(NCB)
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የፕሮጀክቶች ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት ለካራ ቆሬ ዕቃ ግምጃ ቤት የአጥር ግንባታ የእጅ ስራ በዘርፉ ከተሰማሩ ደረጃ 8 እና ከዛ በላይ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ ።
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር ፍቃድ ያላቸው የታደሰ የመንግስት ግዥና የንብረት የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡና በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ በኢፌዴሪ አስተዳደር ኤጀንሲ ድህረ ገጽ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፣
- የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የኢ.ኤ.አ. ፕሮጀክቶች ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት ከካቴድራል መብራት ወደ አራት ኪሎ በሚወስደው መንገድ ከኤንሪኮ ኬክ ቤት 150 ሜትር ርቀት በሚገኘው ዋስትና የንግድ ማዕከል 11ኛ ፎቅ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 40,000.00 (አርባ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የዋስትና ጊዜው ከሚያበቃበት ቀን በኋላ 28 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ያለው የባንክ ዋስትና (Bank Guarantee) በአ.ኤ.አ. ፕሮጀክት ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ወይም EEU-PP ስም ተዘጋጅቶ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎኘ በማድረግ እና ጨረታ ቁጥር EEU/ PPM/05/2018(NCB) የሚል ምልክት በማድረግ እስከ ነሐሴ 29 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በኢ.ኤ.አ. ፕሮጀክቶች ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት ዋስትና የንግድ ማዕከል ህንጻ ላይ 1ኛ ፎቅ በመቅረብ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ባይገኙም/ ነሐሴ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ የጨረታ ሰነዱን በ ስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡00-6፡ -00 ከ ሰዓት 7፡00 -11፡00 እና ቅዳሜ ጠዋት ከ 2፡00 – 6፡00 መመልከት ይቻላል ።
- የፕሮግራም ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
- ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር፡- 0111 263 153 መደወል ይችላሉ።
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
የፕሮጀክት ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት