Your cart is currently empty!
የሀድያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዞኑ ባህል ቱሪዝም መምሪያ ለሀድያ ብሔር ዘመን መለወጫ ያሆዴ ክብረ በዓል አከባበር የሚሆን ባህላዊ አልባሳት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 22, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀድያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዞኑ ባህል ቱሪዝም መምሪያ ለሀድያ ብሔር ዘመን መለወጫ ያሆዴ ክብረ በዓል አከባበር የሚሆን ባህላዊ አልባሳት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት ተጫራቾች፡-
1ኛ, በመስከ የታደሰ ንግድ ፈቃድ
2ኛ, የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር
3ኛ, የዕቃ አቅራቢነት ሰርተፍኬት ያላቸው ድርጅቶች፤
በሀድያ ዞን ፋ/መምሪያ ቢሮ ቁጥር 17 በአካል በመቅረብ የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እንድትገዙና ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 30,000/ሠላሳ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ሲሆን የጨረታ መወዳደሪያ መምሪያው ባዘጋጀው ፎርማት ላይ ብቻ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የመወዳደሪያ ፖስታዎችን ኦርጅናልና ኮፒ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 17 ላይ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እንድታስገቡና ጨረታውም በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በ4፡30 ላይ የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የእረፍት ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 046 178 4281/ 046 555 2337 ደውሎ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የሀድያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ሆሳዕና