በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ የከፍተኛ ባለሌላ ማዕረግተኛ ማሠልጠኛ ት/ቤት የፅህፈት ዕቃዎችን፣ የፅዳት ዕቃዎችን፣ የኤሌክትሪክ እቃዎችን፣ የቧንቧ ዕቃዎችና የተለያዩ አልባሳት በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 22, 2025)

ብሄራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ የከፍተኛ ባለሌላ ማዕረግተኛ ማሠልጠኛ /ቤት የፅህፈት ዕቃዎችን ፣የፅዳት ዕቃዎችን፣ የኤሌክትሪክ እቃዎችን የቧንቧ ዕቃዎችና የተለያዩ አልባሳት በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም፦

1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈለ ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ እና ከግዥ ኤጀንሲ የተሰጠ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማስረጃ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

2. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋ ሲያቀርቡ የእቃው ሙሉ ስም የተሰራበትን ሀገር እና የጥራት ደረጃውን/specification/ አሟልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡

3. ጨረታው የሚከናወነው በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ስነስርዓት እና ይህንኑ አስመልከቶ የኢ... መንግስት ባወጣው በአዲሱ የግዥ አዋጅ ቁጥር 1333/2017 መመሪያ 1073/2017 መሰረት ብቁ ለሆኑ ተጫራቾች ነው።

4 የጨረታ ሰነዶች ማስገቢያ የሚሆነው ጦላይ የከፍ/ባለሌላ ማዕረግተኛ //ቤት ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ቢሮ ቁጥር 28 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከነሀሴ 16 ቀን 2017 . እስከ ነሀሴ 30 ቀን 2017 . ከቀኑ 800 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተ/ 4 በተገለጸው አድራሻ ሆኖ በቢሮ ቁጥር 28 ነሀሴ 30 ቀን 2017 . ከቀኑ 800 ሰዓት ተዘግቶ 830 ሰዓት ይከፈታል።

6. ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ/ ብር ብቻ በመከፈል በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ጦላይ ከፍ ባለሌላ ማዕረግተኛ //ቤት ቢሮ ቁጥር 28 ግዥ ዴስከ ማግኘት ይችላሉ፡፡

7. በተጨማሪ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የከፍ ባለሌላ ማዕረግተኛ ማሰልጠኛ /ቤት /MINSTRY OF NATIONAL DEFENCE SINOR NON COMMISION OFFICER TRAINING SCHOOL/ በሚል በማንኛውም ህጋዊ ባንክ 50,000.00 /የሃምሳ ሺህ ብር/ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

8. አሸናፊው ድርጅት በጨረታ ሠነድ ላይ የተጠቀሱትን ዕቃዎች አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ውል ካሰረ 20 ቀናት ውስጥ እቃውን አጠናቆ ጦላይ ማሰልጠኛ /ቤት ማስገባት ይኖርበታል፡፡

9. ተጫራቾች ሰነዱን በሚገዙበት ወቅት ማሰልጠኛ /ቤቱ ያቀረባቸውን የእቃ ሳምፕሎች በማየት ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡ ሌላ ማሰልጠኛ /ቤቱ ያላቀረባቸው የእቃ ሳምፕሎች ካሉ አሸናፊ ድርጅቶች ሳምፕሎችን ውል በሚሰሩበት ወቅት ለመስሪያ ቤቱ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

10. መስሪያ ቤታችን የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

11. ተጫራቾች በንግድ ስያሜያቸው ስም የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ አካውንት ቁጥር ሊኖራቸው ይገባቸዋል፡፡

12. በጨረታ አሸናፊ የሚሆኑት ድርጅቶች የውል ማስከበሪያ ዋስትና ሲያስይዙ ካሸነፉት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 10%/አስር ፐርሰንት/ የባንክ ጋራንት ወይም c.p.o ማስያዝ የሚችሉ መሆን አለበት፡፡

13. ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያው ላይ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ ማድረግ አለበት፡፡

14. ተጫራቾች አሸናፊ የሚሆኑት ለእያንዳንዱ እቃ በሚያቀርቡት እቃ አነስተኛ ዋጋና ጥራት ያለው እቃ ይሆናል፡፡

15. ተጫራቾች ሰነዳቸውን ሲያቀርቡ ኦርጅናልና ኮፒ ብለው መለየት አለባቸው፡፡

አድራሻ፡ኦሮሚያ ክልል ዞን ጅማ ቦተር ጦላይ ወረዳ ላይ ይገኛል

ለተጨማሪ ማብራሪያ በቢሮ ስልክ ቁጥር 011 388 0012 በሞባይል ስልክ ቁጥር 09 37 99 14 75 / 09 47 98 16 39/ 09 10 44 96 13 ይደውሉ።

በሀገር መከከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ የከፍተኛ ለሌላ ማዕ/ማሠ//ቤት