የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


Addis Zemen(Aug 22, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍ/ባለመብቶች እነ ተናኜ አምዴ እና በፍ/ባለዕዳ / የውብዳር የሺ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ /ቤት በመ/ቁጥር 99198 በየካቲት 13 ቀን 2016 . እና በኮ// 101264 በሚያዝያ 03 ቀን 2016 . 23/04/2017 . 17/06/2017 . በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በግንቦት 11 ቀን 2017 . በለሚ ኩራ /ከተማ ወረዳ 5 የሆነው መኖርያ ቤት RELO/89/1389 የሆነው ቤት አስመልክቶ የቦታው ስፋት 150 / የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 3,757,644 (ሦስት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሃምሳ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ አርባ አራት ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም 20 ቀን 2018 . በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 830 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬከቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ//ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ከፍል ድረስ ጠዋቱ 330 ሰዓት ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራቾች በሚጫረቱበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ 1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ//ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን 15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታው ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ ዳይሬክቶሬት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም /ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *