Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ ጉባኤ እግዚያአብሄር ቤተክርስቲያን እርዳታና ልማት ማኅበር 1ኛ ደረጃ ፍርኖ ዱቄት ባለ 10 ኪ.ግ እና ባለ 1 ሊትር ፈሳሽ ዘይት ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 22, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ጉባኤ እግዚያአብሄር ቤተክርስቲያን እርዳታና ልማት ማኅበር መንግስታዊ ያልሆነ በጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዕቃዎች፣ 1ኛ ደረጃ ፍርኖ ዱቄት ባለ 1ዐ ኪ.ግ እና ባለ 1 ሊትር ፈሳሽ ዘይት ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም፡_
ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በአዲስ አበባ ወሎ ሰፈር በኢትዮ ቻይና መንገድ ካስ ታወር ሕንፃ (ወንጌላዊት አካባቢ) አጠገብ ባለው መንገድ ጉባኤ እግዚያአብሄር በሚገኘው ቢሯችን ድረስ በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ። ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ሲመጡ የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የግብር ከፍይ መለያ ቁጥር መያዝ ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን ከግዥ ከፍል ዘወትር በሥራ ሰዓት ማግኘት ይችላሉ። ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በድርጅታችን የኢትዮጵያ ጉባኤ እግዚአብሄር ቤተክርስቲያን እርዳታና ልማት ማኅበር ስም በአዋሽ ባንክ ወይም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ 20,000 (ሀያ ሺ ብር ብቻ) cpo አሠርተው ከዋጋ መቅረቢያው ሰነድ ጋር በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስገባት ወይም ጨረታ የሚከፈትበት ዕለት ይዘው መቅርብ ይኖርባቸዋል።
በዚህ መሠረት ተጋባዥ ተጫራች ድርጅቶች ተጫራቾች የፋይናሻል ዶከሜንት ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ ታሽገው መቅርብ አለባቸው። ፍርኖ ዱቄት 1 ኪሎ ሳምፕል ማቅረብ አለባቸው።
የሚያቀርቡትን የዘይት ዓይነት (ብራንድ) መግለፅ አለባቸው።
በጨረታ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ክብ ማህተም እና ፊርማ ማድረግ እንዲሁም ስርዝ ድልዝ ቢያጋጥም በፊርማ ማረጋገጥ ይኖርበታል።
ልማት ማኅበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ነሐሴ 28/12/2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09 67 006 339 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ጉባኤ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን የእርዳታና ልማት ማኅበር