የአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 8 ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሠራት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 22, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 8 ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ ቁጥር 001/2018 በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታች የተዘረዘሩትን ሎቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሠራት ይፈልጋል።

  • ሎት 1 የጽሕፈት መሳሪያ
  • ሎት 2 የፕሪንተር እና የፎቶ ኮፒ ቀለም
  • ሎት 3 የፅዳት ዕቃ
  • ሎት 4 የደንብ ልብስ
  • ሎት 5 ካሜራ
  • ሎት 6 የመኪና ጎማ
  • ሎት 7 የአትክልት ዘር
  • ሎት 8 የፕሪንተርና ፎቶ ኮፒ ጥገና
  • ሎት 9 የቢሮ መገልገያ ጥገና
  • ሎት 10 የኤሌክትሪክ ጥገና
  • ሎት 11 የህትመት ሥራ
  • ሎት 12 የሀይገር ኪራይ
  • ሎት 13 መለስተኛ አይሱዙ ኪራይ መጫረት የምትፈልጉ የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባችኋል።

ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ መስክ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸውና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ተርን ኦቨር ታክስ /TOT/ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

የመንግስት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የተሟላ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያገለግል ሎት 1,2,3,4,5,6 ለእያንዳንዱ ሎት ብር 10,000.00/አስር ሺህ ብር/ እና ሎት 7,8,9,10,11,12,13 ለእያንዳንዱ ሎት ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ/ ብር በአ/ክ/ከ/ወ/08/ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም ሲፒኦ በማሠራት ከጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

የጨረታ ሰነዱ አንደኛ ፎቅ ፋይናንስ ጽቤት የሚገኝ ሲሆን ለእያንዳንዱ ሎት በማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ/ ብር በመግዛት ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።

ጨረታው የሚቆይበት ጊዜ 10 የሥራ ቀናት ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳው አዳራሽ ይከፈታል። የጨረታ ሰነዱን የገዙትን ኦርጅናልና ኮፒ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው።

ከጨረታው ሰነድ ውጪ ተሞልቶ የሚመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

ጨረታው ሰነድ ተሞልቶ አንደኛ ፎቅ ፋይናንስ ጽቤት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ገቢ ይደረጋል።

መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ፦ የሚያስገቡት ዋጋ ሻትን ጨምሮ መሆን አለበት

አድራሻ ፡- ራስ አምባ ሆቴል ፊት ለፊት ቤሊየር ወረድ ብሎ አ/ክ/ከ/ወ/08 ወጣት ማዕከል

የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 8 ፋይናንስ ጽ/ቤት