Your cart is currently empty!
በከምባታ ዞን በአዲሎ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በኅብረተሰብ ተሳትፎ ለሚገነባው አስተዳደር የቢሮ ሕንፃ ግንባታ G+1 slab ድረስ የጉልበት ዋጋ በጨረታ አወዳድሮ በጉልበት ዋጋ ማስገንባት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 23, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የግንባታ ጉልበት ዋጋ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር 001/2017
በከምባታ ዞን በአዲሎ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በኅብረተሰብ ተሳትፎ ለሚገነባው አስተዳደር የቢሮ ሕንፃ ግንባታ G+1 slab ድረስ የጉልበት ዋጋ በጨረታ አወዳድሮ በጉልበት ዋጋ ማስገንባት ይፈልጋል።
ስለሆነም፡
- ደረጃቸው BC/GC 5 እና ከዚያ በላይ፣
- ተጫራቾች በመስኩ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላችሁ፣
- የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢና የታክስ መለያ ቁጥር ያላችሁ የሆናችሁ፣
- በዘርፉ የአቅራቢነት የምዝገባ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የምትችሉ፣
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር ብቻ) ማቅረብ የምትችሉ፣
- ተጫራቾች ለሥራው የተዘጋጀውን ጨረታ ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 800 (ስምንት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ዘወትር በሥራ ቀናት በፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 05 ቀርበው መውሰድ ይችላሉ።
- የመጫረቻ ሰነዶቻችሁን ቴክኒካልና ፋይናንሻል አንድ አንድ ኦሪጂናልና ሁለት ሁለት ኮፒ በማሸግና በአንድ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ ጨረታው በወጣበት በ22ኛው ቀን ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ እስከ 9፡00 ሰዓት ማስገባት አለባቸው፡፡ ነገር ግን በ22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡ በዛው ሰዓት 9፡00 ሰዓት ታሽጎ 9፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡-0916681144/0916101017አዲሎ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በከምባታ ዞን የአዲሎ
ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር