Your cart is currently empty!
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት የኬዝ ሎደር፣ ኤር ትራከር እና ሚኒ ዶዘር መለዋወጫ ዕቃዎች ግዥን ለመፈጸም እንዲቻል በዘርፋ ህጋዊ ፈቃድ ካላቸው ድርጀቶች በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 23, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት የኬዝ ሎደር፣ ኤር ትራከር እና ሚኒ ዶዘር መለዋወጫ ዕቃዎች ግዥን ለመፈጸም እንዲቻል በዘርፋ ህጋዊ ፈቃድ ካላቸው ድርጀቶች በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡-
1. በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፣
3. የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፤
4. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 (አስር ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲፒኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
5. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ (አዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 በመቅረብ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አሥራ አምስት ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በባንክ አካውንት በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
6. የጨረታ ሰነዱን በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ ፋይናንሻል አንድ ኦሪጅናልና ሁለት ኮፒ በመያዝ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡00–4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም ጨረታው ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከረፋዱ 4:30 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል። ይህ ቀን በዓል፤ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል። የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
7. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 046-220-99 63/046-212-13-34
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ