Your cart is currently empty!
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ለከተማ ውስጥ ለሚሰሩ መንገዶች የሚውሉ እና ሬዳሽ ለማምረት የኮንስትራክሽን መሳሪያ አገልግሎት ግዥን በኪራይ ለመፈጸም እንዲቻል በዘርፋ ህጋዊ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 23, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ለከተማ ውስጥ ለሚሰሩ መንገዶች የሚውሉ እና ሬዳሽ ለማምረት የኮንስትራክሽን መሳሪያ አገልግሎት ግዥን በኪራይ ለመፈጸም እንዲቻል በዘርፋ ህጋዊ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚገዙ ዕቃዎች፡-
- ሎደር ባኬት 3ሜኩ
- ኤክስካቫተር ቼን ከነ ጃክ ሀመር
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡-
1. በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣
3. የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣
4. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ) ብር በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲፒኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
5. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ (አዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 በመቅረብ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አሥራ አምስት/ ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
6. የጨረታ ሰነዱን በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ ፋይናንሻል አንድ ኦሪጅናልና ሁለት ኮፒ እና ቴክኒካል አንድ ኦሪጅናልና ሁለት ኮፒ በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 አስራ አምስት ተከታታይ ቀናት በፋይ/ኢኮ/ልማ/ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
11. ጨረታውን በ16ኛው ቀን ከረፋዱ ከ3፡00-4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል እና 4፡00 ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 5 ይከፈታል። ይህ ቀን በበዓላት፣ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል። የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 046-220-99-63/046-212-13-34
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ