Your cart is currently empty!
በምስራቅ ጎጃም አስ/ዞን የደጀን ከተማ አስተዳደር ገን/ጽ/ቤት የጽህፈት መሳሪያ ህጋዊ ነጋዴዎችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 05, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ጎጃም አስ/ዞን የደጀን ከተማ አስተዳደር ገን/ጽ/ቤት ለደጀን ከተማ አስተዳደር ባለ በጀት ሴክተር መ/ቤቶች ለ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚውል የጽህፈት መሳሪያ ህጋዊ ነጋዴዎችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ የንግድ ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ።
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና ስለመከፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /tin number / ተመዝጋቢና ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ።
- በእያንዳንዱ ሎት/ ምድብ ጠቅላላ ግዥው ወይም ዋጋው ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብ/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /vat/ ተመዝጋቢ የሆነና ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍና የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒውንና ኦርጅናል ሰነዶቻቸውን ማቅረብና ማመሳከር ይኖርባቸዋል።
- የሚገዙ እቃዎችን አይነት ዝርዝርና ስፔስፊኬሽን መ/ቤታችን በአማርኛ ቋንቋ ያዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በ100.00 /አንድ መቶ/ የኢትዮጵያ ብር በመግዛት ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችል እና በጨረታው ላይ ችግር ቢከሰትና ጨረታውን ካሸነፈ በኋላ በራሱ ምክንያት ውል ባይፈፅም ያስያዘውን ገንዘብ የሚወረስ መሆኑንና አቅርቦቱን ካሸነፈ ለውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ የሚችል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በኦርጅናል ኮፒ የሚመለከታቸውን ሰነዶች በሙሉ በማድረግ ስርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ በጀርባው ላይ የድርጅቱን አድራሻ ማህተምና ፊርማ በማድረግ በደጀን ከ/አስ/ገ/ፅ/ቤት በግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 18 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባችኋል። ጨረታ በ16ኛው ቀን ጠዋት 3፡00 ላይ ይታሸጋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሁሉም በግ/ፋ/ን አስ/ደ/የስ/ሂደት ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 በግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስ/ሂ/ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 18 ይከፈታል። እለቱ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
- ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም ጽ/ቤቱ የሚከፍት ይሆናል።
- መ/ቤታችን ከሚገዛው እቃ 20% ሃያ ፐርሰንት መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል።
- ተጫራቾች የሚለዩት በእያንዳንዱ ምድብ በሰጡት ጠቅላላ ዋጋ /ሎት/ ይሆናል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ተጠቃሚነታቸው በአዲሱ ግዥ መመሪያ መሰረት ሲሆን ካደራጃቸው መ/ቤት የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በደጀ/ከተገን⁄ ፅ/ቤት በግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 18 ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 776 0024/058 776 1009 በመደወል ማግኘት ይቻላል።
በአብክመ በምስራቅ ጎጃም ዞን የደጀን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት