Your cart is currently empty!
በን/ስ/ላ/ክ/ከ የተሐድሶ የመ/ደ/ት/ቤት በ2018 ዓ.ም. የተለያዩ እቃዎች እና አገልግሎት በመስኩ ከተሰማሩ ተጫራቾች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 04, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥው መለያ ቁጥር 0001/2018
በን/ስ/ላ/ክ/ከ የተሐድሶ የመ/ደ/ት/ቤት በ2018 ዓ.ም. ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች እና አገልግሎት በመስኩ ከተሰማሩ ተጫራቾች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም
- ሎት 1 የደንብ ልብስ የሲ.ፒ.ኦ. መጠን 13,000.00
- ሎት 2. አላቂ የቢሮ እቃዎች እና የማስተማሪያ እቃዎች – የሲ.ፒ.ኦ. መጠን 16,000.00
- ሎት 3. የህክምና እቃዎች–የሲ.ፒ.ኦ. መጠን 1,000.00
- ሎት 4. የጽዳት እቃዎች ልዩ ልዩ እቃዎች ——-የሲ.ፒ.ኦ. መጠን 13,000.00
- ሎት 5. የጥገና እቃዎች የሲ.ፒ.ኦ መጠን 2,000.00 ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት፡–
1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
2. ተጫራቾች የጨረታው ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ.. ከጨረታው ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
3. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በተከታታይ 10/አስር/ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 150.00 (አንድ መቶ ሐምሳ ብር) በመክፈል በን/ስ/ላ/ክ/ከ ተሃድሶ የመጀ/ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 (ሰባት) በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሽገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት በን/ስ/ላ/ክ/ከ ተሃድሶ የመጀ/ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 (ሰባት) ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
5. ጨረታው በአስረኛው ቀን በን/ስ/ላ/ክ/ከ ተሃድሶ የመጀ/ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 7(ሰባት) 11፡30 ሰዓት ታሽጎ በማግስቱ ከጠዋቱ 3፡00 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በን/ስ/ላ/ክ/ከ ተሃድሶ የመጀ/ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 7(ሰባት)ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ሎቶች ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የሚያቀርቡት ናሙና በተግባር ይፈተሻል/
7. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
8. የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
9. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፈባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
10. የጨረታ ሰነዱ በጥንቃቄ መሞላት ሲኖርበት የተሰረዘ እና የተደለዘ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በተጨማሪ ለማብራሪያ ጥያቄ አድራሻ፡– ን/ስ/ላ/ክ/ከ ተሃድሶ የመጀ/ደ/ት/ቤት ወረዳ 12 መድሐኒያለም ቤተክርስቲያን አጠገብ የመ/ቤቱ ስልክ ቁጥር፡– 011-471-0803
በን/ስ/ላ/ክ/ከ የተሐድሶ የመ/ደ/ት/ቤት