Your cart is currently empty!
ሁንዴ ኦሮሞ ግራስሩትስ ዲቨሎፕመንት ኢኒሸቲቭ የግንባታ እና ለቧንቧ ውሃ ዝርጋታ የሚውሉ ግብዓትን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Reporter(Sep 03, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ሁንዴ ኦሮሞ ግራስሩትስ ዲቨሎፕመንት ኢኒሸቲቭ በቦራና ዞን በትግበራ ላይ ካሉት ፕሮጄክቶች ውስጥ አንዱ በCordaid/DRA በተገኘው ድጋፍ የሚተገበር Ethiopian Joint Response” የሚል ፕሮጄክት ነው።
ስለዚህም ድርጅታችን በቦረና ዞን በተለያዩ ወረዳዎች ህብረተሰቡን በኢኮኖሚና በልማት ለማቋቋም የተለያዩ ሥራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል።
በመሆኑም በጨረታ ዶክመንት ውስጥ የሚገኙትን የግንባታ እና ለቧንቧ ውሃ ዝርጋታ የሚውሉ ግብዓትን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህም በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላችሁና የጨረታውን ሰነድ መስፈርት የምታሟሉ አቅራቢ የንግድ ድርጅቶች የጨረታ ሰነዱን 300 ብር በመክፈል ከድርጀቱ መግዛት የምትችሉ ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ የሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ 2% በሁንዴ ግራስሩትስ ዲቬሎፕመንት ኢኒሼቲቭ ስም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ከጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ጋር በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተካታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ መስቀል ፍላወር አከባቢ ቪላ ቬርዴ ሆቴል አጠገብ በሚገኘው ዋና መ/ቤት ማቅረብ ይችላሉ።
የጨረታው ሰነድ ማስገቢያ ቅፅ የሚጠናቀቀው ከላይ በተገለፀው መሠረት በመጨረሻው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሲሆን የሚከፈተው በዚያው ቀን 4:30 ላይ ይሆናል።
ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ – በስልክ ቁጥር ፡– 011 558 4094 / 09 13 39 98 17 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።