Your cart is currently empty!
ዴቭሎፕመንት ስሩ አደልት ኤንድ ነን ፎርማል ኢዱኬችን የትምህርት ቁሳቁሶች እና ንፅህና መጠበቂያ መግዛት ይፈልጋል
Reporter(Sep 03, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የትምህርት ቁሣቁሶች የጨረታ ማስታወቂያ
DAN/0056
ዴቭሎፕመንት ስሩ አደልት ኤንድ ነን ፎርማል ኢዱኬችን (ዳንፌ) መንግስታዊ ያልሆነ ለትርፍ ያልተቋቋመ የሀገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን መንግስት ባወጣው የዳግም ምዝገባ ሥርዓት አጠናቆ በመዝገብ ቁጥር 0045 በመመዝገብ በመላው ኢትዮጵያ በበጎ አድራጎት ሥራ ላይ እንዲንቀሳቀስ የተፈቀደለት ድርጅት ነው። በዚህም መሰረት ድርጅቱ በስሩ ለሚገኙ የፕሮጀክት ተጠቃሚዎች የትምህርት ቁሳቁሶች እና ንፅህና መጠበቂያ ይፈልጋል። ስለዚህ ከታች የተዘረዘሩትን እቃዎች ማቅረብ የሚችሉ ህጋዊ ተጫራቾች ይጋብዛል።
| ተ.ቁ | የትም ህርት ቁሳቁስ | መለኪያ | ጠቅላላ ብዛት | 
| 1 | ደብተር (ባለ 100) | በቁጥር | 28000 | 
| 2 | እስኪሪብቶ (ሰማያዊ) | በቁጥር | 16800 | 
| 3 | እርሣስ (HP) | በቁጥር | 16800 | 
| 4 | ማጥፊያ | በቁጥር | 5600 | 
| 5 | መቅረጫ | በቁጥር | 5600 | 
| 6 | ማስመሪያ (30cm) | በቁጥር | 5600 | 
| 7 | ቦርሳ | በቁጥር | 5600 | 
| 8 | ሳሙና (100 ግራም) | በቁጥር | 5600 | 
| 9 | እንደገና ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል የጨርቅ የፊት ጭንብል | በቁጥር | 5600 | 
| 10 | እንደገና ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል የንፅህና መጠበቂያ ሞዴስ | በሴት | 2800 | 
| 11 | የፕላስቲክ እቃፊ የመማሪያ ቁሳቁሶችን ለማከማቸት) | በቁጥር | 5600 | 
| 12 | ደብተር (ባለ 50) | በቁጥር | 2800 | 
| 13 | እስክርቢቶ | በቁጥር | 700 | 
| 14 | ጠመኔ | በፓክ | 700 | 
| 15 | ዳስተር | በቁጥር | 560 | 
| 16 | ክላሰር | በፓክ | 70 | 
| 17 | ፍሊፕ ቻርት | በቁጥር | 280 | 
| 18 | መስመሪያ (30CM) | በቁጥር | 140 | 
| 19 | ቀስተ ደመና ወረቀት (ባለ ቀለም ወረቀት) | በሪም | 140 | 
| 20 | ማርከር | በፓክ | 280 | 
| 21 | መቀሶች | በቁጥር | 140 | 
| 22 | Wood fix ኮላ | በቁጥር | 280 | 
| 23 | የፕላስቲክ አቃፌ (የመማሪያ ቁሳቁሶችን በማከማቸት) | በቁጥር | 140 | 
- ተወዳዳሪዎች በዘሩ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መስያ ቁጥር /ቲን የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማረጋገጫ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።ተጫራቾች እነዚህን እና ሌሎች ተያያዥነት ያሳቸውን ማረጃወች ኮፒ በማድረገ በጀርባው ማህተም በማድረግ በማጫረቻ ሰነዳቸው ላይ ማካተት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ለተከታይ ለ6 ቀናት ማስትም ከነሐሴ 28 እስከ ጳጉሜ 3 ዓየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ጳጉሜ 4/2017 ከሰዓት 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ጨረታዉ ዳንፌ ዋና መ/ቤት ጀሞ 1 ሳባ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከቀረበው ጠቅላላ ዋጋ 2% በቶክ በድርጅቱ ስም በማሰራት ከጨረታ ዶክመንቱ ጋር በማያያዝ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን ማስትም የዋጋ ሰነዳቸውን በታሸገ ፓስታ አንቨሎፕ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት የትምህርት ቁሣቁሶች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የትምህርት ቁሣቁሶች የሚያቀርቡበት ጊዜ /delivery time/ ውል ከተያዘበት ቀን ጀምሮ በ5 በአምስት/ ተከታይ የስራ ቀናት ውስጥ ብቻ ይሆናል።
- ተጫራቾች ሰነዱን ከዳንፌ ዋናው መ/ቤታችን በጋዜጣዉ ላይ በተጠቀሱት ቀናት መሰረት ከጠዋት 3:00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰአት በኋላ 7፡00 ሰዓት ሰከ 10፡00 ሰአት የሚያገኙ ይሆናሲ የጨረታ ሰነዱን ጅሞ 1 ሳባ ሕንፃ 1ኛ ፎቅ ከፋይናንስ ክፍስ መውሰድ ይችላሉ።
- ድርጅቱ የተሻስ ስማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
ለበለጠ መረጃ፦ በስልክ ቁጥር +251 93 621 0808/ 09 07 36 54 44