Your cart is currently empty!
በአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት በደ/ጎን/አስ/ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የቤት የጨረታ ማስታወቂያ አውጥቷል
Addis Zemen(Sep 03, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
አፈ ከሳሽ ….እነ ይታየው ፍቃዴ /5ሰዎች/
አፈ/ተከሳሽ እነ ደጀኔ አበራ /4 ሰዎች/ መካከል ስላለው የገንዘብ ክስ ክርክር ጉዳይ በ4ኛ ተከሳሽ ስም ማለትም በሙሉ ገበያ አየለ ስም የተመዘገበ ቤትና ቦታ በደ/ታቦር ከተማ ቀበሌ 04 ቀጋ ወሀ ተብሎ ከሚጠራው ቦታ በአዋሳኝ ምስራቅ ቁጥር 388 በምዕራብ 386 ሰሜን ቁጥር 401 ደቡብ መንገድ ስፋቱ 200 ካ/ሜ ላይ በሆነ ቦታ ላይ ያረፈ ቤት በጨረታ በመነሻ ዋጋ 900080.2 /ዘጠኝ መቶ ሺህ ሰማኒያ ብርከ 2/100 ሳንቲም/ በሆነ መሸጥ ስለተፈለገ የጨረታ ማስታወቂያው አየር ላይ የሚቆየው ለተከታታይ 30 ቀናት ሲሆን ይህም ከመስከረም 05 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 04 ቀን 2018 ዓ.ም ይሆናል ፡፡ ጨረታው የሚከናወነው የፍ/ቤቱ ሀራጅ ባይ የደ/ታቦር ከ /ቀ 04 አስ/ጽ/ቤት እና የቀበሌው ምድብተኛ ፖሊስ ባለበት በ05/02/2018 ዓ.ም ቤቱ ከሚገኝበት ቦታ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ሲሆን የጨረታ አሸናፊው ለፍ/ቤቱ የሚገለፀው ጥቅምት 06 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ይሆናል፡፡ የጨረታ አሸናፊው ያሸነፈበትን ገንዘብ 1/4ኛ ወዲያኑ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ፍ/ቤቱ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት በደ/ጎን/አስ/ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት