Your cart is currently empty!
በደቡብ ም/ህ/ክ/መ በቤንች ሸኮ ዞን በሼ/ቤ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በዋን ዋሽ ፕሮግራም ለማዝ ጤና ጣቢያ ደረቅ ቆሻሻ ማቃጠያ ግንባታ፤ ዣዥ ጤና ጣቢያ አጠባበቅ ጣቢያ የእጅ ፓምፕ የውሃ ግንባታ እና ጥ/እሸት ጤና ጣቢያ አጠባበቅ ጣቢያ የእጅ ፓምፕ የውሃ ግንባታ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 03, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር፡ 01 ዋሺ ፕሮግራም
በደቡብ ም/ህ/ክ/መ በቤንች ሸኮ ዞን በሼ/ቤ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2017/18 የበጀት ዘመን በዋን ዋሽ ፕሮግራም ለማዝ ጤና ጣቢያ ደረቅ ቆሻሻ ማቃጠያ ግንባታ፤ ዣዥ ጤና ጣቢያ አጠባበቅ ጣቢያ የእጅ ፓምፕ የውሃ ግንባታ እና ጥ/እሸት ጤና ጣቢያ አጠባበቅ ጣቢያ የእጅ ፓምፕ የውሃ ግንባታ ከዚህ በታች የተዘረዘረው መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
- ደረጃ 8ከዚያ በላይ ለደረቅ የቆሻሻ ግንባታ G.C/B.C ለእጅ ፖምፕ ግንባታ WC ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ሰነድ ለመግዛት በሚመጡበት ጊዜ ለበጀት ዓመቱ የሚያገለግል የብቃት ማረጋጋጫ፣
- የንግድ ፍቃድ የምዝገባ ወረቀት፣ ቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁ/ር እና
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት በማቅረብ በሼ/ቤ/ወ/ገ/ጽ/ቤት የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ 600 ብር /ስድስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይጠበቅባቸዋል።
- የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ በተገቢው ሁኔታ ማቅረብ የሚችል
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15,000 ብር /አስራ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማሲያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቹ የገዙበትን ሰነድ /ፋይናሻል ቴክኒካል/ ከላይ የተዘረዘረው አስፈላጊ የሆኑትን መረጃዎች አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ እያንዳንዱንና ለየብቻ በሰም በማሸግ በጥቅል በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው።
- እያንዳንዱ ፖስታ በታሸገ በማህተም መምታት በሙሉ አድራሻ በመጻፍ እና በመፈረም ኦርጅናል ኮፒ የሚል ጸሁፍ በግልጽ በሚታይ ቦታ መጻፍ አለበት።
- ተጫራቹ ሁሉንም የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዶች ላይ የተጫራቾች ህጋዊ ፊርማ እና እንዲሁም የደርጅቱ ማህተም መኖር አለበት።
- እያንዳንዱ ፖስታ የሚወዳደሩበትን የሥራ ቦታ፣ የተጫራች አድራሻ እና የተወካይ ስልክ ቁጥር እና የውክልና ማስረጃ መጻፍ አለባቸው።
- ይህ ጨረታ በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጂናል እና ሁለት ኮፒ በማድረግ ማስገባት አለባቸው፡
- ጨረታው የሚታሸገው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን በሼ/ቤ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮች በተገኙበት ይታሸጋል።
- ጨረታው የሚከፈትበት ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን በሼ/ቤ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮች በተገኙበት ይከፋታል።
- ሎት 1 ማዝ ቀበሌ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የደረቅ የቆሻሻ ማቃጠያ ግንባታ
- ሎት 2 ዣዥ ቀበሌ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ እና ጥ/እሸት ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የእጅ ፓምፕ ግንባታ
- በሎት የተከፋፈሉት ስራዎች በእያንዳንዳቸው በፓስታ ላይ በማሸግ የተወዳደረበትን የስራ ዓይነት ፖስታው ላይ መጻፍ አለባቸው።
- ጨረታው ዋጋ ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ዕለት ለ90/ዘጠና ቀናት ብቻ ይሆናል።
- የግንባታው የሳይት ቦታ በሼይ ቤንች ወረዳ ማዝ ፤ዣዥ እና ጥእሸት ቀበሌ ጤና ጣቢያ ገቢ ውስጥ ይገኛሉ።
- የግንባታው የማጠናቀቂያ ጊዜ የውል ስምምነት ከተፈፀበት ቀን ጀምሮ በ3 ሦስት ወር ወይም በ9ዐ በዘጠና) ቀናት ውስጥ ይሆናል።
- የጨረታው ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ዕለት ጀምሮ ለ3 ሦስት ወር ወይም 90 /ዘጠና/ ቀናት ብቻ ይሆናል።
- በተጫራቾች ተሞልተው የሚቀርቡ የግንባታ ሥራ የመወዳደሪያ ሀሳብ ደጋፊ ሰነዶች በግልፅና በጥራት መግለፅ አለባቸው፤ ይህም የሚሆነው ካላይ በተገለፀው የግዥ መለያ ቁጥር መሠረት ሆኖ ከተገለጹት ጉዳዮችና ሁኔታዎች ጋር የተጣጣመና ተቀባይነት ያላቸው መሆን አለባቸው፣
- በተጫራቾች ተሞልተው የሚቀርቡ የመወዳደሪያ ሀሳብ እና ሌሎችም ተጨማሪ ማረጋገጫዎች የሚመለከተው ኃላፊ ፊርማና ማህተም ካልተደረገባቸው የቀረበው የመወዳደሪያ | ሀሳብ ሊሰረዝ ይችላል።
- ጽ/ቤታችን የዚህን ግንባታ የሚፈፅመው የተዘረዘሩትን ሁኔታዎችና የቴክኒካ መመዘኛዎች ከሚያሟሉት መካከል በመንግስት በግዥ አፈጻጸም መመሪያ መሰረት ዝቅተኛ ዋጋ ላቀረበው ተጫራች የግዥ ግንባታ ትዕዛዝ በመስጠት ይሆናል፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ ለ15 (ለአስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ይሆናል።
- አሸናፊ ተጫራች የውሉን 10% የውል አፈጻጸም ዋስትና በተጨማሪ የማህበራዊና የአካባቢ ደህንነት የውሉን 10% የአፈፃጸም ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል።
- አሸናፊ ተጫራች የውሉን 30% የቅድመ ከፍያ ሊጠይቅ ተመጣጣኝ የባንክ ጋራንቲ ሲያቀርብ የሚከፈል ይሆናል።
- በጨረታው ላይ ለሚነሱት ማንኛውም ጥያቄዎች በጽ/ቤት አድራሻ በኩል ምላሽ ማግኘት ይቻላል።
- የጽ/ቤቱ አድራሻ ሼይ ቤንች ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት የወረዳ አስ/ር ም/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገኛል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0917161765/0917959630
በደ/ም/ህ/ክ/መ/ሼይ ቤንች ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
cttx Building Construction cttx, cttx Construction and Water Works cttx, cttx Electrical, cttx Finishig Works cttx, cttx Pumps, cttx Water Construction cttx, cttx Water Engineering Machinery and Equipment cttx, cttx Water System Installation cttx, cttx Water Well Drilling cttx, Electromechanical and Electronics cttx, Motors and Compressors cttx