Your cart is currently empty!
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በ2018 በጀት ዓመት ለመንገድ ግንባታ ግብዓት የሚሆን ኮንክሪት ቱቦ (RC-pipe) ባለ 1000 ሚ.ሜ እና ባለ 1200 ሚ.ሜ ኮንክሪት ቱቦ (RC-pipe) በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 03, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥው መለያ ቁጥር፡– አአከመባ/ግብዓት/ቡ-2/003/2018
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በ2018 በጀት ዓመት ለመንገድ ግንባታ ግብዓት የሚሆን ኮንክሪት ቱቦ (RC-pipe) ባለ 1000 ሚ.ሜ እና ባለ 1200 ሚ.ሜ ኮንክሪት ቱቦ (RC-pipe) በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ተ.ቁ |
የዕቃው ዓይነት |
ብዛት |
ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ |
የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
1 |
RC-pipe (ኮንክሪት ቱቦ) ባለ 1000 ሚ.ሜ |
25,888
|
60 ቀን
|
መስከረም 8 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት |
መስከረም 8 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 5፡30 ሰዓት
|
500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) |
2 |
RC-pipe (ኮንክሪት ቱቦ) ባለ 1200 ሚ.ሜ |
1,190
|
ስለዚህ
- ተጫራቾች አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም በመንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድህረገፅ (WWW.PPA.gov.et) መመዝገብ ይኖርባቸዋል። እንዲሁም ተጨማሪ መቅረብ ያለባቸው ሰነዶች በጨረታ ሰነዱ በተገለፀው መሰረት ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ መጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ መዝጊያ ተብሎ ከላይ አስከተጠቀሰበት ቀን ድረስ ባሉት የስራ ቀናት ከባለሥልጣኑ መ/ቤት የፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 135 መውሰድ ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ Certified payment (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የባንከ ዋስትና ከሆነ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና/Unconditional Bank Guarantee) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከላይ በሰንጠረዥ በተገለፀው መሰረት ብር 500,000.00/ አምስት መቶ ሺህ ብር/ ነው። ከባንከ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።
- ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ከላይ በሰንጠረዡ የጨረታ መዝጊያ ተብሎ እስከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በባለሥልጣኑ መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከላይ በሰንጠረዡ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በባለሥልጣኑ ዋና መ/ቤት ይከፈታል።
- ባለስልጣን መሰሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ሳርቤት ፑሽኪን አደባባይ ሳይደርስ
ስልክ ቁጥር፡– 011-372-0825/011-371-4103
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን