በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ስር የሚገኘው መንጃ ያዥ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለስራ የሚያገለግሉ ደንብልብስ፣ አላቂ የቢሮ ዕቃ፣ የህትመት ስራ፣ አላቂ የህክምና ዕቃ፣ አላቂ የትምህርት ዕቃዎች፣ ሌሎች አላቂ እቃዎችና አቅርቦቶች፣ የትራንስፖርት አገልግሎት ኪራይ፣ ለፕላንት ማሽነሪ እድሳትና ጥገና፣ ለጭነት አገልግሎት ኪራይ፣ ለፕላንት ማሽነሪ መሳሪያ መግዣ እና ለህንፃ ለቁሳቁስ ተገጣጣሚ መግዣ በግልፅ ጨረታ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 03, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

አንደኛ ዙር ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ስር የሚገኘው መንጃ ያዥ አጠቃላይ 2 ደረጃ ትምህርት ቤት 2018 በጀት ዓመት ለስራ የሚያገለግሉ ደንብልብስ፣ አላቂ የቢሮ ዕቃ፣ የህትመት ስራ፣ አላቂ የህክምና ዕቃ፣ አላቂ የትምህርት ዕቃዎች፣ ሌሎች አላቂ እቃዎችና አቅርቦቶች፣ የትራንስፖርት አገልግሎት ኪራይ፣ ለፕላንት ማሽነሪ እድሳትና ጥገና፣ ለጭነት አገልግሎት ኪራይ፣ለፕላንት ማሽነሪ መሳሪያ መግዣ፣ ለህንፃ ለቁሳቁስ ተገጣጣሚ መግዣ በግልፅ ጨረታ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት፦

1. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (tin number) ያላቸው

2 የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ

3. የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና በሚወዳደሩበት ዘርፍ የዘርፍ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ

4. ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

5. ክሊራንስ፦የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት ስለ ግብር አከፋፈል የሚሰጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

6. ተጫራች በአቅራቢነት ፍቃድ ስለመመዝገባቸው (ONLINE Registration ) ከኢ... የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ማቅረብ ግዴታ አለባቸው።

7. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በአስረኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ላይ ተዘግቶ በዚያው ቀን 730 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባለብት ይከፈታል።

8. ተጫራቾች በየሎቱ በባንክ የተረጋገጠ የጨረታ ማስከበሪያ CPO በትምህርት ቤቱ ስም (Temenja Yazh G/Secondary School በተጠቀሰው ሎት ለደንብ ልብስ 5,000ብር፣ ለአላቂ የቢሮ ዕቃ 7,500 ብር፣ የህትመት ስራ 1,500 ብር፣ አላቂ የህክምና ዕቃ 2,000 አላቂ የትምህርት ዕቃዎች 8,500 ብር፣ ሌሎች አላቂ ዕቃዎችና አቅርቦቶች 5,000 ብር፣የትራንስፖርት አገልግሎት ኪራይ 3,722.40ብር፣ ለፕላንት ማሽነሪና ጥገና 1750 ብር ለጭነት አገልግሎት ኪራይ 2,000ብር፣ ለፕላንት ማሽነሪ መሳሪያ መግዣ 10,000 ብር፣ ለህንፃ ለቁሳቁስ ተገጣጣሚ መግዣ 2,000 ብር CPO የጨረታ ማስረከቢያ የማስያዝ ግዴታ አለባቸው ይህን ያላሟሉ ተጫራቾች በቀጥታ ከውድድር ውጭ ይሆናሉ።

9. በእያንዳንዱ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ወይም ገፅ ወይም ሎት ላይ የተወዳዳሪው ድርጅት ማህተም እና ፊርማ በማኖር ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህን ያላሟሉ ተጫራቾች ህጋዊነቱን እና ኦርጅናልነቱን ለመለየት ስለማያስችል ይህን ያላሟሉ ተጫራቾች በከፊል ወይም በሎት ወይም በገፅ ወይም ሙሉ በሙሉ ከውድድር ውጭ ይሆናል።

10.ማንኛውም ተጫራቾች ፋይናሺያሉን ለብቻ በአንድ ፖስታ በማሸግ እና የፋይናሺያሉን ኮፒ በሌላ አንድ ተጨማሪ ፖስታ በማሸግ ቴክኒካሉን ለብቻ በአንድ ፖስታ በማሸግ በአጠቃላይ በሶስት ፖስታ ብቻ በማድረግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ይህን ያላሟላ ተጫራች ውድድር ውጭ ይሆናል።

11. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ ስርዝ ድልዝ የሌለበትና በጨረታ ሰነድ ዋጋ ማቅረቢያው ቦታ ላይ የተሞላ መሆን አለበት ይህ ካልሆነ መስሪያ ቤቱ ስርዝ ድልዝ ያለበት እና በውል ለመለየት አዳጋች የሆነ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ወይም ሎት ወይም ገፅ በከፊል ውድቅ ያደርገዋል።

12. ተጫራቾች ናሙና በሚያስፈልጋቸው እቃዎች ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸውበጨረታ ሰነዱ ላይ ከተጠቀሰው የፍላጎት መግለጫ ውጭ የሚቀርቡ የናሙና ዓይነቶች ድርጅቱ የማይቀበል መሆኑን እንገልፃለን ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚተኩ ማናቸውም ዓይነት ናሙና ድርጅቱ ሊቀበል አይችልም።

13. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለአስር ተከታታይ የስራ ቀናት በተቋሙ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር ሶስት (03) በመቅረብ 100 (አንድ መቶ) ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

14. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃ ውል በገቡ በአስራ አምስት የስራ ቀን ውስጥ ገቢ የማድረግ ግዴታ አለባቸው።

15. የህትመት ስራን በተመለከተ ውሉ የሚፀናው ለአንድ ዓመት የህትመት አገልግሎት የመስጠት ግዴታ አለበት።

16. ለትራንስፖርት አገልግሎት እና ለለጭነት አገልግሎት ውሉ የሚፀናው ለአንድ ዓመት ብቻ አገልግሎት የመስጠት ግዴታ አለበት።

17. ትምህርት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

18. አድራሻ፦ ጠመንጃ ያዥ የባቡር ፌርማታው ፊትለፊት በእምነት ባርና ሬስቶራንት በስተጀርባ 300 ሜትር ገባብሎ

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፦ 0114 703 870 ይደውሉ።

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 የጠመንጃ ያዥ አጠቃላይ 2 ደረጃ ትምህርት ቤት