በሰ/ሸዋ /ዞን የባሶና ወራና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ ቤት የጽህፈት መሳሪያ፣ የመኪና ጎማ ከነከመናዳሪውና የመኪና መለዋወጫ እቃዎች እና የእንሰሳት መድሃኒትና መገልገያ መሳሪያዎች ተጫራቾች ጋር ውል በመፈፀም መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 02, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ /ዞን የባሶና ወራና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ላሉ //ቤቶች 2018 በጀት ዓመት

  • ሎት1የጽህፈት መሳሪያ
  • ሎት 2የመኪና ጎማ ከነከመናዳሪውና የመኪና መለዋወጫ እቃዎች
  • ሎት 3- የእንሰሳት መድሃኒትና መገልገያ መሳሪያዎች

በዘርፉ የተሰማሩ ቅራቢዎችን በማሳተፍና በማወዳደር ዝቅተኛ ዋጋ ከሰጠው ድርጅት አሸናፊ ተጫራቾች ጋር ውል በመፈፀም መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ፡የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።

  1. የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃቸውን ማቅረብ የሚችሉ።
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TN ያላቸው።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን መሞላት የሚገባውን መረጃ ሁሉ በትክከል በመሙላት እና በመፈረም አንድ ኦርጅናል ፖስታ የራሳቸውን ፊርማና አድራሻ ተፅፎበት ለእያንዳንዱ ሎት ለየብቻው በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 2:30 እስከ 1130 ድረስ የጨረታ ሰነዱን ከባሶና ወራና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ ቤት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200(ሁለት መቶ ብር ብቻ) ከቢሮ ቁጥር 20 በመግዛት 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን 430 ላይ ይከፈታል።ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይታገድም።
  4. ከተዘረዘሩት እቃዎች መካከል ከፋፍሎ መሙላት አይቻልም፡፡ ሁሉም እቃዎች መሞላት አለባቸው::
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በቁርጥ ለጽህፈት መሳሪያ 25000(ሃያ አምስት ሺህ ብር) ለመኪና ጎማ ከነከመናዳሪውና የመኪና መለዋወጫ እቃዎች 30,000(ሰላሳ ሺህ ብር)እና ለእንሰሳት መድሃኒትና መገልገያ መሳሪያዎች 15000(አስራ አምስት ሺህ ብር) በባሶና ወራና ወረዳ ገንዘብ /ቤት ስም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ ማሲያዝ አለባቸው::
  6.  የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል።
  7. በሎት 3 ላይ የተጠቀሰው የእንስሳት መድሀኒት እና መገልገያ መሳሪያዎች ግዥን በተመለከተ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ጅምላ አከፋፋዮች ብቻ በጨረታው ላይ የሚሳተፉ ይሆናል።
  8. ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ በኋላ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ 10% የውል ማስከበሪያ በባሶና ወራና ወረዳ ገንዘብ /ቤት ስም ማስያዝ እና ውል መዋዋል ይኖርባቸዋል።
  9.  /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-63750-23 ደውለው መረዳት ይችላሉ።

የባሶና ወራና ወረዳ ገጓዘብ /ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *