በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ትም/ፅ/ቤት የጄኔራል ዋቆ ጉቱ 1ኛ ደረጃ ቁ-2 ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የደንብ ልብስ፣ የፅህፈት መሣሪያዎች፣ ህትመት፣ የትምህርት መሣሪያዎች፣ የፅዳት መሣሪያዎች፣ ለማሽነሪ እና ለተገጣጣሚ ቋሚ፣ እድሳት እና ጥገና አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 02, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ 

የጨረታ ቁጥር 001/2018

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ትም/ፅ/ቤት የጄኔራል ዋቆ ጉቱ 1ኛ ደረጃ ቁ-2 ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1. የደንብ ልብስ
  • ሎት 2. የፅህፈት መሣሪያዎች
  • ሎት 3. ህትመት
  • ሎት 4. የትምህርት መሣሪያዎች
  • ሎት 5. የፅዳት መሣሪያዎች
  • ሎት 6. ለማሽነሪ እና ለተገጣጣሚ ቋሚ
  • ሎት 7 እድሳት እና ጥገና አገልግሎት

በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።

  1. የታደሰ የዘርፉን ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል።
  2. የዘመኑን ግብር ስለመክፈሉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
  4. ተጫራቾች የግዥና ንብረት ማስወገድ ባለስልጣን ባወጣው የአቅራቢዎች ዝርዝር ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
  5. ተጫራቾች የመንግስት ግብር የከፈሉና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆኑን የሚገልፅ አግባብነት ያለው ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
  6. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በጄ/ዋቆ ጉቱ 1ኛ ደረጃ ቁ-2 ት/ቤት ግዥ ክፍል በመቅረብ ከሎት 1 እስከ ሎት 7 ላሉት ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት ቁጥር 1 ሰላሳ ሽህ ብር ብቻ (30,000) ሎት 2 ሀያ ሽህ ብር ብቻ (20,000) ሎት 3, ሶስት ሽህ ብር ብቻ (3,000) ሎት 4 (ስምነት ሽህ (8,000) ሎት 5 ሰላሳ አምስት ሽህ ብር ብቻ (35,000) ሎት 6 ሃያ ሽህ ብር ብቻ (20,000) እና ሎት 7ሶስት ሽህ ብር ብቻ (3,000) ብር ሲሆን በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በጄኔራል ዋቆ ጉቱ 1ኛ ደረጃ ቁ-2 ት/ቤት ስም አዘጋጅቶ ማቅረብ የሚችል። 
  8. በሽርክና ማህበር ተደራጅቶ የሚሰሩ አቅራቢዎች የተጠየቀውን ዋስትና የሚያቀርቡት ደብዳቤ ከአደራጃቸው አካል በት/ ቤቱ አድራሻ ማቅረብ የሚችል።
  9. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ይታሸጋል በዕለቱ የስራ ሰዓት 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቦታ ይከፈታል።
  10. ተጫራቾች በሙሉ በሚወዳደሩበት ሎት ላይ ጨረታው ከመከፈቱ 1 ቀን ቀደም ብሎ በት/ቤቱ ግዥ ክፍል ናሙና ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  11. ተጫራቾች በገዙት ጨረታ ሰነድ ባለው የዋጋ መሙያ ቦታ ላይ ቫትን ጨምሮ በግልጽ ሞልቶ በማህተም አስደግፎ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  12. ተጫራቾች በተወዳደሩበት ዋጋ አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው በኋላ በ 7 ተከታታይ በስራ ቀናት ውስጥ ቀርበው ከአሸነፉት ጠቅላላ ዋጋ 5% ማስከበሪያ በት/ቤቱ ስም በቼክ በሲፒኦ ለግዥ ክፍል በማቅረብ ውል መግባት አለባቸው።ያስያዙትን ገንዘብ ተመላሽ የሚሆነው በውሉ መሰረት የሚጠበቅባቸውን ግዴታ ከተወጡና ውሉን ተመላሽ ሲያደርጉ ነው።
  13. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  14. ዕቃውን ሲያስገቡ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት ሲሆን ከሰዓት ደግሞ 7፡00 ሰዓት እስከ 9፡00 ድረስ መሆኑን እያሳውቅን ከተጠቀሰው ሰዓት ውጭ የሚመጡ ከሆነ የማናስተናግዳቸው መሆኑን እንገልፃለን።
  • አድራሻ፣ ኢ.አ ኮ ቀ/ ክ/ከተማ ወረዳ 07 ጄ/ዋ/ጉ/1ኛ ደ/ቁ-2 ት/ቤት አለም ባንክ እሳት አደጋ ፊት ለፊት
  • ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥሮች 09 12 25 52 29/ 09 10 19 03 76

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ትም/ፅ/ቤት የጄነራል ዋቆ ጉቱ 1ኛ ደረጃ ቁ_2 ት/ቤት