Your cart is currently empty!
ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 02, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የዕቃና አገልግሎት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2018
የሎት ዓይነት
- ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያና ተዛማጅ እቃዎች
- ሎት 2 የፅዳትና ተዛማጅ ዕቃዎች
- ሎት 3.የኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ ተዛማጅ ዕቃዎች
- ሎት 4 የኮምፒዩተር ዕቃዎች
- ሎት 5 የህንፃ መሳሪያና የግንባታ ዕቃዎች
- ሎት 6 የቋሚ ዕቃዎች
- ሎት 7 የህትመት ሥራዎች
- ሉት 8 የደንብ ልብስ
- ሎት 9 የደንብ ልብስ ስፌት
- ሎት 10 የመኪና እቃዎች
- ሎት 11 ልዩ ልዩ የዕፅዋትና የጓሮ አትክልት ዘር፣ የዕፅዋት ችግኝ
- ሎት 12 ቆሎና ውሃ
- ሎት 13 መስተንግዶ ጥሬ ዕቃዎች
- ሎት 14 የቤተ ሙከራና የቤተ መዘከር ዕቃዎች
- ሎት 15 ሜትሮፖሎጂ ዕቃዎች
- ሎት 16 ፍራሽ
- ሎት 17 የእስፖርት ዕቃዎች
- ሎት 18 የህፃናት መፅሐፍት
- ሎት 19 የተለያዩ ፎቶኮፒና ፕሪንተር ጥገና
ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ባቀረበው ጨረታ ላይ ለመካፈል የዘመኑ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ፣ በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገበበት የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የታደሰ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ እና በፌደራል ግዥ ንብረት አስተዳደር ድረ-ገፅ ላይ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ በዘርፉ የተመዘገቡ መሆኑን የሚገልፅ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
1. የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/ በባንከ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣ በአነስተኛ እና ጥቃቅን ተደራጅተው ለሚረቱ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያው እና የውል ማስከበሪያው ሲፃፍ በተደራጁበት ዘርፍ መፃፍ አለባቸው፤
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ በየሎቱ የተጠመሩትን የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል ከፋይናንስ ዳይሬክቶሬት መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ቀደም ሲል ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ፣ እንዲሁም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም በተጨማሪም ናሙና ማምጣት የሚቻለው የመጀመሪያ የሰነድ ግምግማ ተጣርቶ ውጤት ከታወቀ በኋላ የሚቀርብ ይሆናል፤
4. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን ሲያስገቡ በነጠላ ዋጋና በጠቅላላ ዋጋ መሆን ይኖርበታል። ስሌት ሲሰላ ስህተት ቢኖረው መ/ቤቱ የሚወስደው ነጠላ ዋጋውን ይሆናል። እንዲሁም የጨረታ ዋጋ በሚያስገቡበት ወቅት ማዕከሉ በሸጠው ሰነድ ብቻ መሆን አለበት በተጨማሪም ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ እና ተጨማሪ ፅሑፎች ማስገባት በጨረታው ላይ ተቀባይነት የለውም፤
5. ተጫራቾች ለመወዳደር የሚያስገቡት ዋጋ የሚቆይበት ጊዜ 90 ቀን መሆን ይኖርበታል፤ አጭር ጊዜ መስጠት ከውድድር ውጭ ያደርጋል፤
6.ከላይ የተጠቀሱትን ለጨረታ የሚያስፈልጉ ማስረጃዎች በባንከ በተመሰከረለት ቼክ (CPO)፣ (ቴክኒካል) ሰነዶች ኦርጂናል ለብቻ በአንድ ፖስታ እና ቴክኒካል ሰነዶች ኮፒ ለብቻ በአንድ ፖስታ በማድረግ በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ ፊርማ እና የድርጅቱ ማህተም ተደርጎ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
7. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን (ፋይናንሻል) ሰነዶች ኦርጂናል ለብቻ በአንድ ፖስታ እና ፋይናንሻል ሰነዶች ኮፒ ለብቻ በአንድ ፖስታ በማድረግ በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ ፊርማ እና የድርጅቱ ማህተም ተደርጎ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
8. ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን የጨረታ ሰነዶች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 10 /አሥር የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
9. የጨረታው አሸናፊ የውል ማስከበሪያ ከአሸነፉት ጠቅላላ ዋጋ 10% አሥር በመቶ/ (CPO) በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል፤
10. ጨረታው በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ሆኖም የመክፈቻው ቀን በዓል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፤
11. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፤
12. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር፡- 011 154 7226 ደውለው ያነጋግሩ።
ህንፃ ቁጥር – 2 1ኛ ፎቅ ላይ
አድራሻ፡- ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 በፅዮን ሆቴል 800 ሜትር ገባ ብሎ ልዩ ስሙ አጣሪ ሰፈር ባለው የማዕከሉ ጽ/ቤት
ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል