Your cart is currently empty!
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቱሪዝም ኮሚሽን የገልማ አባ ገዳ ማዕከል ለካፍቴሪያ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ መፈጸም ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 04, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቱሪዝም ኮሚሽን የገልማ አባ ገዳ ማዕከል ለካፍቴሪያ አገልግሎት የሚውሉ ከታች በተዘረዘረው መሰረት በንግድ ዘርፉ የተሰማሩ ሕጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ መፈጸም ስለሚፈልግ ተፈላጊውን መስፈርት የምታሟሉ ድርጅቶችን / ግለሰቦችን ለ6 (ስድስት) ወር ውል በመግባት ግዥ መፈጸም መግዛት ስለሚፈልግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል /ጥሪ ያደርጋል/።
ተ.ቁ |
የዕቃዎቹ ዓይነት ዝርዝር |
ሞዴል/መለያ/ |
መለኪያ |
ብዛት |
የአንድ ዋጋ(ብር) |
መግለጫ |
1 |
ነጭ ማኛ ጤፍ |
1ኛ ደረጃ ንጹህ |
በኪ.ግ |
|
|
|
2 |
ቀይ ጤፍ |
1ኛ ደረጃ ንጹህ |
በኪ.ግ |
|
|
|
3 |
የዳቦ መጋገሪያ ማሽን |
|
በቁጥር |
|
|
|
4 |
32 Trays Electric Rotary bread Oven |
Specification :
|
በቁጥር |
|
|
|
5 |
Heavy Duty 32 Trays Electric Rotary Rack Oven for Bread |
|
በቁጥር |
|
|
|
በዚሁ መሠረት
1. ተጫራቾች በጨረታ ለመካፈል ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑና ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN Number) የምከር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ/ በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሠነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት (15) ተከታታይ ቀናት በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቱሪዝም ኮሚሽን የገልማ አባ ገዳ ማዕከል ጽ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 110 የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ / በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
4. የጨረታ ሠነዱ ይህ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስራ አምስተኛው (15)ኛው ተከታታይ ቀናት ይሸጥና በአስራ ስድስተኛው (16)ኛው የስራ ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት ከቀኑ 8፡30 ይከፈታል።
5. አሸናፊው ድርጅት ለውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ላይ አስር ከመቶ(10/100) በባንክ በተረጋገጠ CPO ማሰያዝ አለበት።
6. የውል ማስከበሪያውም አሸናፊው ድርጅት ዕቃዎቹን በውሉ የጊዜ ገደብ አስገብቶ እስኪያጠናቅቅ ድረስ ተይዞ የሚቆይ ይሆናል።
7. ተጫራቾች አሸናፊ የሆነባቸውን ነጭ ማኛ ጤፍ እና ቀይ ጤፍ ለማቅረብ ለስድስት ወር ውል መፈረም ይጠበቅባቸዋል።
8. ተጫራቾች አሸናፊ የሆነባቸውን እቃዎች በራሳቸው የትራንስፖርት ወጪ ጭነው አዳማ ገልማ አባ ገዳ ማዕከል ጽ/ቤት ድረስ በማቅረብ ማስረከብ ይኖርባቸዋል።
9. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን በተናጠል በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ የድርጅቱ ማህተም አርፎበት መ/ቤቱ ለዚሁ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በጨረታው የመክፈቻ እለት ማስገባት አለባቸው።
10. ሌሎች ዝርዝር ማብራሪያዎች ከሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ።
11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
ማሳሰቢያ፡– የዳቦ መጋገሪያ ማሽኑን ካቀረብነው እስፔስፍኬሽን ውጭ የተሻለ ከተገኘ በአማራጭነት ማቅረብ ይቻላል።
ስልክ ቁጥር፡– 022 112 4565/ 022 212 9255 ደውለው አስፈላጊ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቱሪዝም ኮሚሽን የገልማ አባ ገዳ ማዕከል