Your cart is currently empty!
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የወረባቦ ወረዳ ግዥ ንብረት አስ/ ቡድን በ2018 በጀት ዓመት ለወረባቦ ወረዳ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የመኪና መለዋወጫ ፋስት ሙቪንግ፣ የሞተር ዘይት፣ የቀላል ተሽከርካሪ መኪና ጎማ እና የመኪና እቃ በግልጽ ጨረታ በሎት ድምር አወዳድሮ አሸናፊዎችን በመለየት መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 07, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ወረ/ወረ/ግ/ን/አስ/ 001/2017
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የወረባቦ ወረዳ ግዥ ንብረት አስ/ ቡድን በ2018 በጀት ዓመት ለወረባቦ ወረዳ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የመኪና መለዋወጫ ፋስት ሙቪንግ ሎት1፣ የሞተር ዘይት ሎት 2 ፣ የቀላል ተሽከርካሪ መኪና ጎማ ሎት 3 እና የመኪና እቃ ሎት 4 በግልጽ ጨረታ በሎት ድምር አወዳድሮ አሸናፊዎችን በመለየት መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
1. ተጫራቾች አግባብ ያለው የንግድ ስራ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/TI/ ያላቸውና የሚታይ ኮፒ በማድረግ በፖስታ አሽገው ማቅረብ የሚችሉ፣
2. የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር / እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
3. ተጫራቾች ከላይ በተራ ቁጥር 1 እስከ 2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶችው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው ።
4. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
5. በጨረታው ለመሣተፍ ለሚፈልጉ ጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከ 2/13/2017 ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰአት መግዛት ይችላሉ።
6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከ2/13/2017 እስከ 16ኛው ቀን በ12/1/2018 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር – በእያንዳንዱ ሎት በመለየት ኦርጅናል ኮፒ ሁለት ሁለት ፖስታ በማዘጋጀት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ በወረባቦ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 ማስገባት ይጠበቅባቸዋል። የሞተር ዘይትን በተመለከተ ከተቀመጠው ናሙና ውጭ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም።
7. ጨረታው በ16ኛው ቀን በ 12/1/2018 ዓ.ም በ 5፡00 ሰዓት ይዘጋል።
8. ጨረታው በ16ኛው ቀን በ12/1/2018 ዓ.ም በ 5፡30 ሰዓት ተጫራቾች ሆነ ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ተጫራቾች ፊት በወረባቦ ወረዳ፤ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 በግልጽ ይከፈታል።
9. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፋቸው እቃዎች በተጠየቀው መሰረት ውለታ በመውሰድ ኦርጂናል እቃዎችን ብቻ በመለየት ወረባቦ ወረዳ እቃውን በጠየቁት ባለሙያዎች – የእቃውን ጥራት በማረጋገጥ ወረባቦ ወረዳ በየንብረት ክፍሉ ገቢ በማድረግ ገቢ ለሆኑት እቃዎች ከፍያ መውስድ አለባቸው፡፡
10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድቦንድ/ የሚወዳደሩበት እቃ ጠቅላላ ዋጋ 2% በእያንዳንዱ ሎት በመለየት በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ መሂ-1 በመቁረጥ ከጨረታ ፖስታው ጋር አሽገው ማቅረብ አለባቸው።
11. በመጫረቻ ሰነድ ላይ ከሰፈሩት የውል ቃሎችና ሁኔታዎች ጋር መሰረታዊ ልዩነት ያለው ምግብ ማቅረብ ከጨረታ ተሳታፊነት ያሰርዛል።
12.በሚገዛው ግዥ ላይ መ/ቤቱ 20% የመጨመር 20% የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። የተጫራች መመሪያ ሳይገነጠል አያይዞ ማቅረብ ግዴታ ነው።
14.በነጠላ ዋጋ ሆን ተብሎ የተጋነነ ስርዝ ድልዝ መኖር ከጨረታ ተሳታፊነት ያሰርዛል።
15. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች ለሚወዳደሩበት አቅርቦት ተጨማሪ ማስረጃ ቢያስፈልጋቸው 033 221 00 25 ወይም በግንባር በመቅረብ ወይም ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 መረጃ ማግኘት ይቻላል።
16. የጨረታው መክፈቻ ቀን የበዓል ቀን ቅዳሜና እሁድ ከገጠመ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
በደቡብ ወሎ ዞን የወረባቦ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት