Your cart is currently empty!
በሲዳማ ክልል የሎካ አባያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለሴክተሪ መ/ቤቶች የሚያስፈልጉ አላቂ የፅህፈት መሳሪያ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 07, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ክልል የሎካ አባያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለሴክተሪ መ/ቤቶች የሚያስፈልጉ አላቂ የፅህፈት መሳሪያ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በዚህ ዘርፍ የተሰማራችሁ ህጋዊ ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ16 የስራ ቀናት ለወረዳው ገቢዮች 50 ብር በመክፈል ሰነዱን ከግ/ፍን/አስ/ስራ ሂደት መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
ማሳሰቢያ
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የገበሩ፣ የቫት ተመዝጋቢ፣ ቲን ቁጥር ያላቸውን የብቃት ማረጋገጫ፣የአቅራቢነት ምዝገባ ወረቀት ያላቸው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ10 የስራ ቀናት ውስጥ በአየር ላይ የሚውል ይሆናል።
- ተጫራቾች በማጭበርበር ወንጀል ያልተመዘገቡ፣
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ 5000 CPO ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታውን ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻቸው በማድረግ እና ኤንቨሎፕ በማሸግ በ11ኛ ቀን በሲዳማ ክልል ሎካ አባያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከሚገባበት ቀን ድረስ ከቀኑ 3፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ11ኛ ቀን ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
- 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ የሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
- ጨረታው ያሸነፈው አካል/ድርጅት ዕቃውን እስከ ቦታው ድረስ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በክፍል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በሲዳማ ክልል የሎካ አባያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት