Your cart is currently empty!
በሸገር ከተማ አስተዳደር የገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት ለመንግስት ሰራተኞች እና ለህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሪክ ባስ (service) መኪና በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 16, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ የገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት ወገን ክ/ከተማ ለመንግስት ሰራተኞች እና ለህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሪክ ባስ (service) መኪና በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተገለጸውን መመሪያ (መረጃዎች በማቅረብ) ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤
- አቅራቢዎች ዝርዝር ተርታ የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤
- ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት (15) ተከታታይ የስራ ቀናት እና በስራ ሰዓት ለሰነድ የማይመለስ ብር 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር) በገላን ክ/ ከተማ ገቢዎች ባለስልጣን ጽ/ቤት በመክፈል ሰነዱን ከገላን ክ/ከተማ ዝ ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር (ሰነድ) ዋና እና ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኢንቨሎፕ / በፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት (15) ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ በገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት ባዘጋጀነው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ታሽጎ (ተዘግቶ) ልክ በዚሁ ቀን በ4፡35 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት ውስጥ ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል። ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስ በሪያ ዋስትና ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ጨረታውን አሸናፊነቱ ከተገለፀላቸው በኋላ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው በኋላ ውል ካልፈፀሙና የውል ማስከበሪያ ካላስያዙ የጨረታ ማስከበሪያው መንግስት ገቢ ይሆናል።
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተገለፀው መሰረት የተጫረተበት ዕቃ ናሙና Sample ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል።
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ለይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም።
- የመወዳደሪያ በጨረታ ሰነዱ በተዘረዘረው መሠረት ተሞልቶ ማቅረብ ይኖርበታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-445 0182 በመደወል እና በአካል ተገኝተው መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
በሸገር ከተማ አስተዳደር የገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት