Your cart is currently empty!
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለዋና መ/ቤት ጥገና አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የማሽን መለዋወጫ ዕቃዎች ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 16, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE/SP/138/2025
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለዋና መ/ቤት ጥገና አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የማሽን መለዋወጫ ዕቃዎች ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
| ተ.ቁ | የስራ ዝርዝር | የጨረታ ቁጥር | የጨረታ መዝጊያ ቀን | የጨረታ መክፈቻ ቀን | 
| 1 | የተለያዩ የማሽን መለዋወጫ ዕቃዎች | DCE/SP/138/2025 | 21/01/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 | 21/01/2018 ዓ ም ከጠዋቱ 04:15 | 
ስለሆነም
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የታደስ ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 50,000 (ሀምሣ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም ከታወቀ ባንክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሠነዱ በተጠቀሰው ብዛት እና ስፔስፍኬሽን መሠረት መሆን ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ቃሊቲ ቶታል ስታዲየም ጀርባ ወይም ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ት/ቤት አጠገብ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋናው መስሪያ ቤት የግዥ እና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሠነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ መስከረም 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 04:00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው መስከረም 21 ቀን 2018ዓ.ም ከጠዋቱ 04፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ቡድን ቢሮ ይከፈታል።
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡ አድራሻ፡– ቃሊቲ ቶታል ስታዲየም ጀርባ ወይም ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ት/ቤት አጠገብ የቀጥታ ስልክ ቁጥር ቁጥር 0114-40-34-34/33
ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72 WWW.dce-et.com /Email፡ info@dce-et.com
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ