ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የኔትወርክ እቃዎች/ለኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኔትወርክ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን ከአቅራቢ ድርጀቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 17, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ 

የጨረታ ቁጥር _ኅብኮን 04/2018

ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተገለጹትን የኔትወርክ እቃዎች/ለኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኔትወርክ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን ከአቅራቢ ድርጀቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማለትም፡

.

የሚገዛው እቃ አይነት

መለኪያ

ብዛት

1

Cisco catalyst c9300-48p Network switch

pcs

02

2

Cisco catalyst c9300-24p network switch

pcs

05

3

10000 VA APC smart-UPS

pcs

02

4

Extra Hard disc

pcs

02

5

32 GB USB Flash

pcs

03

6

Full Copper Cat 6A UTP Network Cable

Roll (305m)

(305m) (1)

7

Industrial Crimped Ethernet 5-meter full copper Cat 6A UTPP NETWORK CABLE

pcs

50

በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለጹትን የጨረታ መወዳደሪያ መስፈርቶችን የሚያሟላ ማንኛውም አቅራቢ ድርጅት በጨረታው መወዳደር ይችላል።

  1. በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ወይንም የዘመኑ የተሰጠ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር TIN No ያላቸው እና የሞሉት ዋጋ 200,000 ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና ተጫራቾች የኮርፖሬሽናችን ስም የተሠራ ማለትም ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በሚል የተዘጋጀ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 100,000 ብር /አንድ መቶ ሺህ ብር ብቻ/ የጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ የሚከፈል በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ዋስትና ከጨረታ ዶክመንቱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመቁጠር በ15ኛው ከቀኑ 900 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ 9፡30 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ ወይም የበዓላት ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል
  3. የጨረታ ሰነዱን ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በኮርፖሬሽናችን ገንዘብ ያዥ ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
  4. ኮርፖሬሽናችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  5. የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ የኔትወርክ እቃዎች ዝርዝር ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ጋር የተያያዘ መሆኑን እንገልፃለን።
  6. ውድድሩ ከቫት ጋር በጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ነው። ስለሆነም ሁሉም ተወዳዳሪዎች የተዘረዘሩትን እቃዎች ዋጋ መሙላት ይጠበቅባቸዋል። ከተዘረዘሩት እቃዎች አንዱን ወይንም ከዚያ በላይ ያልሞላ ተወዳዳሪ ካለ ከውድድር ውጭ ይደረጋል።
  7. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፦ 058-320-3576መደወል ይችላሉ።

ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *