Your cart is currently empty!
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት የድርጅቱ ሰራተኞች የሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጥ ተሽከርካሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል
Reporter(Sep 17, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCDE 001/2018
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት የድርጅቱ ሰራተኞች የሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጥ ተሽከርካሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት፡–
- ማንኛውም ተጫራች ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን እና የታክስ ክፍያ መለያ ቁጥር (TIN) የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ ስለመሆናቸው በግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ታክስ ክሊራንስ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ የውጪ አገር ተጫራቾች በሚሆኑበት ጊዜ በተቋቋሙበት አገር የተሰጣቸውን የኩባንያ ምዝገባ ወረቀት ወይም ፈቃድ ወዘተ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱ በድርጅታችን ፋይናንስ ዴስክ መውሰድ ይጠበቅባችኋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በTOR በተያያዘው ዝርዝር መሠረት መሆን ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ከተገለፀው ቀንና ሰዓት በፊት በድርጅቱ የግዥ ዴስክ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ቅዳሜ፣እሁድ ወይም የህዝብ በአል ቀን ከሆነ ቀጣይ ወዳለው የስራ ቀን ይተላለፋል።
- የጨረታ ማስከበሪያ እንደ ተጫራቹ ምርጫ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ወይም በባንክ የተሰጠ የተረጋገጠ ቼክ(CPO) ብር 5,00.00(አምስት ሺ ብር) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ከመስከረም 7 ቀን 2018 እስከ መስከረም 16 ቀን 2018 ዓ.ም. አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን መስከረም 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የመክፈቻ ስነ–ስርዓት ይካሄዳል ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በአከፋፈት ሂደት ባይገኙም የጨረታው የአከፋፈት ሂደት አያግደውም።
አድራሻ፡– የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 011 896 06 33/011 896 06 23
አድራሻ ካሳንቺስ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጀርባ ከዚህ ቀደም ስኳር ኮርፖራሽን
የነበረበት የኪያሜድ ኮሌጅ ህንጻ ግራውንድ ላይ