Your cart is currently empty!
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ጋራዥ አገልግሎት፣ የሜካፕ እቃዎች፣ የሳውንድ ሲስተም፣ ሞባይል፣ ከለር ፕርንተር እና የጄኔሬተር መለዋወጫ እቃዎች ግዥ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 19, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ አንድ
በጨረታ ቁጥር ኢሚ.ኔ.በ.ግ.ጨ. 004/2018 ዓ.ም በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት የሚፈልግ በመሆኑ በጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ፡–
- ሎት 1. ጋራዥ አገልግሎት ግዥ
- ሎት 2. የሜካፕ እቃዎች ግዥ
- ሎት 3. የሳውንድ ሲስተም ግዥ
- ሎት 4. የሞባይል ግዥ
- ሎት 5. ከለር ፕርንተር ግዥ
- ሎት 6. የጄኔሬተር መለዋወጫ እቃዎች ግዥ
በጨረታ ቁጥር አ.ሚ.ኔ.በ.ግ.ጨ. 004/2018 ዓ.ም በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት የሚፈልግ በመሆኑ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ፡–
1, በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉና የገቢዎች ከሊራንስ ያላቸው፣
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉና በግዥ አቅራቢነት የተመዘገቡ፣
3. ተጫራቾች በሚያቀርቡት እያንዳንዱ ሰነድ እና በፓስታ ላይ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማቸውን ማኖር ይጠበቅባቸዋል።
4. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ ለእያንዳንዱ
- ሎት 1. ጋራዥ አገልግሎት ግዥ 100,000 ብር
- ሎት 2. የሜካፕ እቃዎች ግዥ 20,000 ብር
- ሎት 3. የሳውንድ ሲስተም ግዥ 50,000 ብር
- ሎት 4. የሞባይል ግዥ 50,000 ብር
- ሎት 5. ከለር ፕርንተር ግዥ 50,000 ብር
- ሎት 6. የጀኔሬተር መለዋወጫ እቃዎች ግዥ 60,000 ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
5. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ቢሮ ቁጥር 6 ለሰነዱ ክፍያ በጋዜጣ በወጣ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 28 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
6. ጨረታው ሚዲያ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች/ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 ይከፈታል። ሆኖም ግን የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን ለመክፈት አያግደውም። የመክፈቻው ዕለት በዓል/ ዕረፍት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።
7. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን ዋናውንና ኮፒውን /ቴክኒካል ኦሪጅናልና ኮፒ፣ ፋይናንሻል ኦሪጂናልና ኮፒ/በተለያየ ፖስታ በማሽግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
8. በአንዱ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው።
9. በጨረታ ያሸነፈ ተጫራች ከመ/ቤታችን ጋር ጨረታውን እንዳሸነፈ ካወቀበት ጊዜ አንስቶ በ15 ቀናት ውስጥ በሲፒኦ የጠቅላላ ዋጋውን 10 በማስያዝ ውል መዋዋል ይኖርበታል።
10. ተቋሙ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡–
- የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ 5 ኪሎ ቅድስት ማሪያም ቤ/ክርስቲያን ከማህበረ ቅዱሳን ጀርባ ያለው ሕንፃ
- ለበለጠ መረጃ ስልክ 0111116382 መደወል ይችላሉ።
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ