Your cart is currently empty!
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን ግዢ መፈፀም ይፈልጋል
Addis Lessan(Sep 20, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዢ መለያ ቁጥር 001/2018
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በጳጉሜ 1 ህትመት ላይ በወጣው የጨረታ ማስታወቂያ ላይ በተፈጠረው የዓመተ ምህርት ስህተትና ህትመቱ መታተም የነበረበት በአዲስ ልሳን ጋዜጣ መሆን ሲገባው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ስለታተመ እንዲሁም የበጀት ዓመቱ ላይ የ2017 በጀት ዓመት ተብሎ የታተመው ስህተት በመሆኑ በ2018 በጀት ዓመት በሚል የተስተካከለ መሆኑን እያሳወቅን በተለያዩ ሎቶች ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳደሮ ግዢ መፈፀም ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት
- ሎት 01 የጽኅፈት መሳሪያ (ስቴሽነሪ) እቃዎች
- ሎት 02፡– የደንብ ልብስ
- ሎት 03፡– የጽዳት እቃ
- ሎት 04፡– የሰራተኞች ካፌ አገልግሎት
- ሎት 05፡– የትራንስፖርት አገልግሎት
- ሎት o6፡– የዲኮር አገልግሎት
- ሎት 07፡– የህትመት አገልግሎት
በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ (የምትችሉ)
- የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ
- በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና የሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ያካተተ እና የቀረበው ነጠላ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ጨምሮ መሆኑን መግለጫ መስጠት አለባቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (tin no) ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለወጣው ጨረታ ለእያንዳንዱ ሎት 1፦ 10,000 (አስር ሺ ብር)፣ ሎት 2፦ 8,000 ( ስምንት ሺ ብር )፣ ሎት 3፦ 7,000 (ሰባት ሺብር)፣ ሎት 4፦ 8,000 (ስምንት ሺ ብር)፣ ሎት 5፦ 5,000 (አምስት ሺ ብር)፣ ሎት 6፦ 4,000 ( አራት ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒዮ (CPO) በአ/ከ/ክ/ከ/ወረዳ 3 ፋ/ጽ/ቤት ስም የተሰራ እና የማይመለስ 100 ብር /አንድ መቶ ብር/ በመያዝ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላል፡፡
- ተጫራቾች በእያንዳንዱ እቃ የሚጫረቱበትን ዋጋ ዝርዝር በመግለጽ በሁለት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ፤ ያቅራቢ ማህተም እና በዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር ላይ ዝርዘሩን የሞላው ኃላፊ በእያንዳንዱ ዋጋ በተሞላበት የጨረታ ሰነድ ላይ በየገጹ በመፈረም ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ኦርጅናል እና ኮፒ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- በጥቃቅን የተደራጁ ተጫራቾች ካደራጃቸው አካል ኦርጅናል የድጋፍ እና አምራች መሆናቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ማምጣት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ዋጋ ማቅረቢያ ሲያቀርቡ ኦርጅናል ደረጃውን የጠበቀና ናሙናውን በአ/ከ/ክ/ከ/ወ/3/ፋ/ጽ/ቤት ግዢ ክፍል በተዘጋጀው የጫረታ ሳጥን ውስጥ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፏቸው እቃዎች ተወዳድረው ካሸነፉ በኋላ ከናሙና ምንም ለውጥ ሳያደርጉ በራሳቸው ወጭ ጭነው የማቅረብና ደረጃውን ያልጠበቀ እቃ ከሆነ መልሰው ትክክለኛውን በቀረበው ናሙና መሰረት የማምጣት ግዴታ አለባቸው፡
- ጨረታው የሚዘጋበት በ10ኛ ቀን 11፡00 ሰዓት ላይ ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ከወጣበት በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት ይሆናል፡፡
- የጨረታ አሸናፊዎች ማሸነፋቸው በጽሑፍ የሚገለጽላቸው ሲሆን ለጨረታው ውል ማስከበሪያ ላሸነፉበት እቃ ዋጋ 10% በማስያዝና ውል የመዋዋል ግዴታ አለባቸው፡፡
- ከፍያ የሚፈጸመው ለሚያቀርቡት እቃ ሙሉ ለሙሉ ንብረት ክፍል ሲያስረክቡ እና የቀረበው እቃ በናሙና መሰረት በጥራቱ ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡
- በጨረታው ሰነዱ ላይ የዋጋ ስርዝ ድልዝ እና ጽ/ቤት የሰጠው እስፔስፊኬሽን መሰረዝ የለበትም፡፡
- ውል ማስከበሪያና ጨረታ ማስከበሪያ ደብዳቤ የምታጽፉ በጥቃቅን የተደራጁ ተጫራቾች የተሰማራቹበትን የንግድ ስራ ዘርፍ የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡
- ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ግዜ 60 ቀናት ነው፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡– መሳለሚያ አማኑኤል ቤተ ክርስትያን ፊት ለፊት ወደ ሰባተኛ በሚወስደው መንገድ በአጂፕ ገባ ብሎ ወረዳው ህንጻ 3ኛ ፎቅ ላይ ይገኛል፡፡
ለበለጠ መረጃ፦ 011 278 1363
አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ፋይናንስ ጽ/ቤት
cttx Advertising and Promotion cttx, cttx Catering and Cafeteria Services cttx, cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Event Organizing and Planning cttx, cttx Hospitality, cttx Interior Design Service and Material cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Printed Advertising Materials cttx, cttx Printing and Publishing cttx, cttx Promotional Items cttx, cttx Rent cttx, cttx Shoes and Other Leather Products cttx, cttx Stationery cttx, cttx Textile, cttx Tour and Travel cttx, cttx Transportation Service cttx, cttx Vehicle cttx, cttx Warehousing, Garment and Leather cttx, Garments and Uniforms cttx, Tour and Travel cttx, Transit and Transport Service cttx