Your cart is currently empty!
የአራዳ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 22, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2018
በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ግዥ ጨረታ።
- ሎት 1. የመኪና ኪራይ ብር 20,000
- ሎት 2 ህትመት ስራ ብር 10,000
- ሎት 3. እስቴሽነሪ ብር 20,000
- ሎት 4. የደንብ ልብስ እና ጫማ ብር 10,000
- ሎት 5.የተለያዩ የመኪና እቃዎች ና የመኪና ጎማዎች ብር 10,000
- ሎት 6.የእጅ ሳሙና ብር 10,000
- ሎት 7 የከተማ ውበት የሚያገለግሉ ግብዓትና የልማት እቃዎች መሳሪያዎች ብር 20,000
- ሎት 8.ለተለያዩ ዝግጅቶች የሚሆን እስቴጅ ሳውንድ ሲስተም እስክሪን ኪራይ ብር 20,000
1. ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ መስክ የዘመኑን ግብር ለመከፈላቸውና የታደሰ የንግድ ምዝገባ እና ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
2. በመንግስት የግዥ ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል TIN No ያላቸውና በገንዘቡና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች ሠነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 /አስር/ የሥራ ቀናት ጊዜ ውስጥ ቀርበው መውሰድ ይችላሉ፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስረከቢያና ዋስትና የሚያገለግል የመጫረቻ ዋጋ ከላይ በተቀመጠው አግባብ በባንክ የተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ በየሎቱ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ቢሮ ማግኘት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
8. ሰነድ የሚመልሱበት በ11ኛው ቀን የስራ ሰዓት ተመልሶ የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ቢሮ ይከፈታል፡፡
9. የጨረታ ሰነዱ ኦርጅናል እና ኮፒተ ሞልቶና ኦርጅናሉ ኮፒው ተለይቶ በፖስታው ላይ ተፅፎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
10. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብና ሌሎችንም ዕቃዎች በቀረበው የፍላጎት መግለጫ መሠረት ዋጋቸውን በአግባቡ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
11. ናሙና ያልቀረበበት የዘገየ በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ እንዲሁም ከጨረታ ሠነድ ውጪ ተሞልቶ የመጣ ሠነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ በጨረታ ሠነድ ክፍል 4, 6 እና 9 የተቀመጡ ግዴታዎች ከሰነዱ ጋር ተሞልተው ያልቀረቡ ጨረታዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
12. አሸናፊ ተጫራቾች 10% የውል ማስረከቢያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
13. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት መጋዘን ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
14. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት እራሳቸው አምርተው ለገቢያ በሚቀርብበት ዕቃ | ምርት/ ካልሆነ በስተቀር የተዘጋጀ ምርት ዕቃ ከግቢያ ላይ ገዝተው ለሚወዳደሩት እያንዳንዱ ምርት ዕቃ እንደማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ እና የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
15. ስርዝ ድልዝ መረጃዎች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
16 መ/ቤቱ ለግዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡- ከአራት ኪሎ ወደ ፒያሳ በሚወስደው መንገድ አዲሱ የክፍለ ከተማ ህንጻ ላይ 3ተኛ ፎቅ በስተቀኝ በኩል ያለው ቢሮ የአራዳ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን
ስልከ ቁጥር፡ 251 900 01 97 39
የአራዳ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን