በወላይታ ሶዶ ከተማ የሚገኘው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት በከተማ ውስጥ ከሚገኙ ጋራዦች የተሸከርካሪ ዓመታዊ ጥገና አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 22, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡01/2018

በወላይታ ሶዶ ከተማ የሚገኘው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ 2018 በጀት ዓመት በከተማ ውስጥ ከሚገኙ ጋራዦች የተሸከርካሪ ዓመታዊ ጥገና አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይኖርባችኋል።

1. በሚወዳደሩበት ዘርፍ አግባብነት ያለውና ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፤ የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ከሚመለከተው አካል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤

2. በፌዴራል ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዌይብ ሳይት የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ከዌይብ ሳይት አትመው ከጨረታ ሰነድ ጋር ማያያዝ የሚችሉ ወይም በክልሎች በአቅራቢነት ስለመመዝገባቸው የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤

3. የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤

4. የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ ይቆያል።

5. ተጫራቾች ጨረታው ከፍት ሆኖ በሚቆይበት ጊዜ ውስጥ በቢሮው የተዘጋጀውንና የጨረታውን ዝርዝር ሁኔታ የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ የንግድ ፈቃዳቸውን በማሳየት ዘወትር በሥራ ሰዓት በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቀርበው የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድና የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በአግባቡ በማዘጋጀት በፖስታ አሽገው ጨረታው ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ በሚቆይበት ቀን እስከ 1125 ሰዓት ድረስ በቢሮው ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6. ጨረታው ክፍት ሆኖ በሚቆይበት የመጨረሻው ቀን 1130 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ቀጥሎ ባለው 16ኛው ቀን 330 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ይከፈታል። 15ኛው እና 16ኛው ቀን የሚውለው ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓላት ቀን ላይ ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 300 ሰዓት ተዘግቶ 330 ሰዓት ይከፈታል።

7. ተጫራቾች የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ ስም ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን ብር 30,000.00 በሲፒኦ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

8. የፋይናንሻል፣ የቴክኒክ ሰነድ እና የሲፒኦ ፖስታ ተለይቶ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጨረታው አየር ላይ መቆያ ጊዜ ከሚያበቃበት የመጨረሻው ቀን ጀምሮ ላሉት 60 ተከታታይ ቀናት የሚያገለግል መሆን ይኖርበታል።

9. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለጸበት 05 ቀናት ውስጥ አሸናፊ የሆነበትን የአገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ በመያዝ 15 ቀናት ውስጥ ውል መግባት የሚችሉ መሆን አለበት።

10. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 046-1-80-50-71 በመደወል ማብራሪያ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *