Your cart is currently empty!
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የባሕር ዳር ሪጅን የከባድ፣ መካከለኛ እና ቀላል ተሽከርካሪዎችን ለ3 ዓመት በሚቆይ ውል ተጫራቾችን አወዳድሮ የጥገና አገልግሎት ማግኘት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 23, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡– ኢኤአ-ባሪ/ግብጨ/006/2018
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የባሕር ዳር ሪጅን የከባድ፣ መካከለኛ እና ቀላል ተሽከርካሪዎችን ለ3 ዓመት በሚቆይ ውል ተጫራቾችን አወዳድሮ የጥገና አገልግሎት ማግኘት ይፈልጋል።
በመሆኑም፡–
ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራና ብቃት ያለው ጋራዥ ጥገና ለማድረግና ለማደስ መወዳደር ይችላል።
ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራና ብቃት ያለው ድርጅት የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በሚከተለው አድራሻ ማግኘት ይቻላል። በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የባሕር ዳር ሪጅን ቢሮ ቁጥር 408 ስልክ ቁጥር 058-320-6999/6775 ባሕርዳር
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማግኘት ይችላሉ።
ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ በዘርፉ ፈቃድ ያላቸዉ፤ የንግድ ስራ ፈቃድ እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ/ VAT/ ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸዉ።
ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO፣ በባንክ ጋራንት ወይም በጥሬ ገንዘብ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ/ ማስያዝ አለባቸዉ።
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ኮፒና ኦርጅናል በማለት እስከተጠቀሰው የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ በተ.ቁ 3 በተገለጸው አድራሻ ድረስ በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
ተጫራቾች ከመንገድና ትራንስፖርት ባለስልጣን የተሰጠ የስራ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል።
ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መሰረት ማቅረብ አለባቸው።
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ባይገኙም በባሕር ዳር ሪጅን ሰፕላይ ቼይን፣ ንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 408 መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል።
ሪጅኑ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የባሕር ዳር ሪጅን