Your cart is currently empty!
ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃላ.የተ.የግል ማኅበር ቡና ማዘጋጃና ማከማቻ የተለያዩ ስራዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 23, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የተለያዩ ጥገና ስራ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ሆቡማማ/04/18
ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃላ.የተ.የግል ማኅበር ቡና ማዘጋጃና ማከማቻ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሥራዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
ሎት 1- የቢሮ መገልገያ ቁሳቁስ (ፕሪንተር፣ፎቶ ኮፒ እና ኮምፒውተሮች) ሲበላሹ ውል በመግባት ጥገና የሚያደርግለት እንዲሁም የ PBX ስልክ መስመር እና ቀፎ ጥገና፣
- ሎት 2-ለድርጅቱ ፋብሪካ የሚሆን (Conventiona Fire Alarm System) ዕቃ አቅርቦትና ገጠማ።
- ሎት-3 Power factor Correction (for 1481.74kw) minimize up to 0.9 or 1.0
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ በሙሉ ከታች የተዘረዘሩትን በማሟላት በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
1. የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና ቲን ቁጥር ያላቸው
2. ለሎት 1 ለጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ እና ለሎት 2 እና 3 ደግሞ ለእያንዳንዳቸው ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
3. ለጨረታው ማስከበሪያ በሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃላ.የተ.የግል ማኅበር/ HORIZON PLANTATIONS PLC/ ስም በባንክ በተረጋገጠ ሲ ፒ ኦ /CPO/ ብቻ ከጨረታው ሰነድ ጋር አብረው ማቅረብ አለባቸው።
4. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃላ.የተ.የግል ማኅበር ቡና ማዘጋጃና ማከማቻ ቢሮ ቁጥር 14 በአካል በመገኘት ስለ ሥራው ሁኔታ ከድርጅቱ ባለሙያዎች ጋር በመነጋገር የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ።
ተ.ቁ |
ሎት |
የጨረታው ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
የጨረታ መዝጊያ ቀን |
የጨ ረ ታ መክፈቻ ቀን |
1 |
ሎት 1 |
የቢሮ ማሽኖች እና PBX ስልክ መስመር እና ቀፎ ጥገና |
10,000 |
መስከረም 28 ቀን 2018 ዓ.ም ሰዓት 9፡00 |
መስከረም 28 ቀን 2018 ዓ.ም ሰዓት 9፡15 |
2 |
ሎት 2 |
ለድርጅቱ ፋብሪካ የሚሆን (Conventional Fire Alarm System) ዕቃ አቅርቦትና ገጠማ |
30,000 |
መስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም ሰዓት 9፡00 |
መስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም ሰዓት 9፡15 |
3 |
ሎት 3 |
Power factor Correction for 1481.74kw (minimize up to 0.9 or 0.1 |
30,000 |
መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም ሰዓት 9፡00 |
መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም ሰዓት 9፡15 |
5. የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ተጫራች ከውድድሩ ውድቅ ይደረጋል፡፡
6. ጨረታው ከላይ በተገለፀው ቀንና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
7. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በተገለጸለት በ3/ሶስት/ ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን የሥራ ውል ተፈራርሞ ሥራውን መጀመር ይኖርበታል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ከጨረታው አሸናፊነት ተሰርዞ ለጨረታው ያስያዘው ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይደረጋል፡፡
8. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 442 37 24 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
አድራሻ፡–ቅ/ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት ወደ ብሔረ ፅጌ መናፈሻ በሚወስደው መንገድ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ
ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃላ. የተ.የግል ማህበር ቡና ማዘጋጃና ማከማቻ