Your cart is currently empty!
ሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ፍትህ ቢሮ ለቢሮ ሥራ አገልግሎት የሚውሉትን የመኪና ጋራዥና ህትመቶችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 23, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ ጨረታ መስያ ቁጥር 001/2018
ሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ፍትህ ቢሮ ለቢሮ ሥራ አገልግሎት የሚውሉትን ዕቃዎች ሎት1 የመኪና ጋራዥና ህትመቶችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
| ሎት.ቁ | የሎት ዝርዝር | የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብር | 
| ሎት 1 | የመኪና ጋራዥ | 50,000 | 
| ህትመቶች | 5,000 | 
- በገንዘብ ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ መሆን አለበት
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በ15 ተከታታይ በሥራ ቀናት ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይከፈታል።
- የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር 300(ሶስት መቶ) በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 220 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት እና ቦታ ይሆናል።
- ቢሮ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። የቢሯችን አድራሻ ሲ/ብ/ክ/መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ አለፍ ብሎ ፍትህ ቢሮ በሚገኝበት ህንጻ በ2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 220 ግዥ ቡድን ክፍል ይገኛል።
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10 ፐርሰንት ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት መ/ቤታችን ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
- ለጨረታው የሰጡት ዋጋ 60 ቀናት ጸንቶ ይቆያል።
በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ፍትህ ቢሮ