Your cart is currently empty!
በሀገር መከላከያ ሚ/ር የምስራቅ ዕዝ ሜንቴናንስ መምሪያ በ2018 በጀት አመት ለዕዙ አገልግሎት የሚውል ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 22, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የምስራቅ ዕዝ ሜንቴናንስ መምሪያ ግልፅ ጨረታ ቁጥር 01/2018 ዓ/ም
በሀገር መከላከያ ሚ/ር የምስራቅ ዕዝ ሜንቴናንስ መምሪያ በ2018 በጀት አመት ለዕዙ አገልግሎት የሚውል
1. የቀላል እና ከባድ ተሽከርካሪዎች መለዋወጫ ዕቃዎች
2. የጀኔተር እና የዳቦ ማሽን መለዋወጫ ዕቃዎች
3. የወታደራዊ ተሽከርካሪ አላቂ መስሪያ ዕቃዎች
በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች ጨረታውን መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ በዚህ መሠረት በተሰማሩበት ስራ ዘርፍ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት ያላቸው ፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ሰርተፍኬት ያላቸው፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ ከ2:30 እስከ 6፡00 ሰዓት እና ከ7፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሐረር ምስራቅ ዕዝ ሜንቴናንስ መምሪያ በሚገኘው ግዥ ዴስክ ቢሮ በመቅረብ ጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡ ጨረታው መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሐረር ቀላዳንባ በሚገኘው ሜንቴናንስ መምሪያ ግዢ ይከፈታል።
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
0920 437 143 / 0913 971 279
በአገር መከላከያ ሚኒስቴር የምስራቅ ዕዝ ሜንቴናንስ መምሪያ ግዥ ዴስክ
ሐረር