Your cart is currently empty!
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ በክልላችን የክትባት ፕሮግራም ለማጠናከር የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች ክትባት ለመስጠት ያስችል ዘንድ የስልጠና ማኑዋል Immunization in practice participant Manual በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት/ ማሳተም ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 23, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ በጤና ሚኒስቴር ከGAVI-CDS 2 በተገኘ ድጋፍ በክልላችን የክትባት ፕሮግራም ለማጠናከር የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች ክትባት ለመስጠት ያስችል ዘንድ የስልጠና ማኑዋል Immunization in practice participant Manual በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ማሳተም ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት፣
| ተ.ቁ | የዕቃው ዓይነት | መለኪያ | ብዛት | ጨረታው አየር ላይ የሚቆይበት እና ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት | ምርመራ 
 | 
| 1 | Immunization in practice participant Manual | በቁጥር | 300 | ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን በ8፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ9፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ | ቢሮው በማያቀርበው ሳምፕል መሠረት | 
በመሆኑም ተጫራቾች
1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ።
2 . የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ከብር 50,000 /ሀምሳ ሺህ/ ብር በላይ ሲሆን የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 /አስር ሺህ/ ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች በሙሉ የመንግስት ግዢ በ e GP በኦንላይን/Online/ ሲስተም የተመዘገበ ብቻ መሆን አለበት።
6. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር/ በጥሬገንዘብ በመክፈል በክልሉ ጤና ቢሮ ግዥና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
7. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋና ዶክመንታቸውን የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ ጨምሮ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ የጨረታ ማስከበሪያውን ሲፒኦ ለየብቻ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ይውላል። ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ታሽጎ ወዲያው 9፡00 ይከፈታል።
8. ጨረታው በቢሮው ግዥና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ለዚሁ ስራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
9. 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት እና ቦታ ይከፈታል፡፡
10. አሸናፊው ድርጅት የጨረታው ውጤት እንደታወቀ ውል የሚፈጽም ሲሆን ያሸነፈውን ህትመት ክልል ጤና ቢሮ ወራቤ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
11. ቢሮው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ 09 16 47 90 21/ 09 11 83 24 63
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ