Your cart is currently empty!
የጋምቤላ ህ/ብ/ክ/መንግስት ፋይናንስ ቢሮ የዜጎች በጀት መረጃ ሠነድ ለማሳተም ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 25, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2018
የተጫራቾች መመሪያ
የጋምቤላ ህ/ብ/ክ/መንግስት ፋይናንስ ቢሮ የዜጎች በጀት መረጃ ሠነድ ለማሳተም ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት በጨረታው መሳተፍ ለሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የሚያሟላ ከሆነ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- ተጫራቾች በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ስለማጭበርበር ሙስና ጉቦ መስጠትና መቀበል ጭምር በኢትዮጵያ ህጎች የተደነገገውን የሚያከብሩ መሆኑን በማረጋገጥ ግዴታ መግባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር አምስት መቶ (500) በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አስራ አምስት/15/ ቀን ድረስ ግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 30 መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የታከስ ከሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ 5 በመቶ በባንክ በተመሰከረለት CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የዋጋ ማቅረቢያና ሌሎች መረጃዎች የያዘው የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ኦርጅናልና ኮፒ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፤ ጨረታው ይህ ጨረታ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 30 ይከፈታል። ይህን የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት መወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውን፤ አድራሻቸውንና የድርጅታቸው ማህተም ማድረግ አለባቸው።
- የጨረታ ማስገቢያ ቦታ ፋይናንስ ቢሮ ግዥና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 30 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ፋይናንስ ቢሮ ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 17 80 47 27 ወይም ቢሮ 30 ቀርበው ይጠይቁ
የጋምቤላ ህ/ብ/ክ/መንግስት ፋይናንስ ቢሮ