Your cart is currently empty!
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የተለያዩ የከባድና የቀላል ጎማዎች ግዥ፣ የደንብ ልብስ እና የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 12, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የጨረታ ማስታወቂያ
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም በያዘው እቅድ መሰረት
- ሎት 1 ለጽ/ቤቱ ተሽከርካሪ መኪናዎች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የከባድና የቀላል ጎማዎች ግዥ
- ሎት2 የደንብ ልብስ
- ሎት 3 የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዢ ለመፈጸም በማቀድ የወጣ ግልጽ የተጫረቾች መመሪያ ነው።
1. በግልጽ ጨረታ ዋጋ ማቅረቢያቸው ላይ የድረጅታቸውን ስም፣ አድራሻችሁን ስልጣን በተሰጠው የድርጅቱ ኃላፊ ፊርማችሁን እና ህጋዊ ማህተማችሁን በማሳረፍና የዋጋ ማቅረቢያውን ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና ካብኔ ጉዳዮች ጽ/ቤት በማለት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2. ለግልጽ ጨረታው የተዘጋጀውን ዝርዝር መግለጫ መመሪያ በደንብ ማንበብ ዋጋ ሲሞላ ከሚደርሰው ስህተት ያድናል፡፡
3. የዋጋ ማቅረቢያ ሲሞላ ስህተት ቢኖረው የግልጽ ጨረታ ሳጥኑ ከመታሸጉ በፊት ስህተቶቹን በጽሑፍ በማረምና በሌላ ፖስታ በማድረግ ፖስታው ላይ የተሻሻለ ወይም የተለወጠ የሚል ጽሑፍ ጽፎ በግልጽ ጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
4. ማንኛውም ተጫራቾች ሌሎች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም አቀርቦ ቢገኝ ከውድድሩ ውጪ ይደረጋል፡፡
5. የግልጽ ጨረታ ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያቸው ላይ የሚሰጡት በግልጽ ጨረታው የሚያቀርቡትን የተወዳደሩበትን ዕቃ ዓይነት፣ መለኪያ እና ያንዱን ዋጋ መሆኑን ካረጋገጡ በኋላ መሆን ይገባዋል፡፡
6. የዋጋ ማቅረቢያ ሲሞላ ስርዝ ድልዝ እንዲኖረው አይፈቀድም፣ በእርሳስ እና በቀይ እስክርቢቶ የተሞላ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
7. ማንኛውም ተጫራቾች ግልጽ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ያቀረበውን ዋጋ መለወጥ፣ ማሻሻል ወይም ውድድሩን ትቻለሁ ቢል ለግልጽ ጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ገንዘብ ይቀጣል እንደ አስፈላጊነቱም መ ቤቱ ወደ ፊት በሚያወጣው ግልጽ ጨረታ ላይ እንዳይሳተፍ ሊያደርግ ይችላል፡፡
8. ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አሸናፊ የሆኑባቸውን የዕቃ አቅርቦት ዋጋ በግልጽ ጨረታ ሰነዶች ላይ ባቀረቡት ዋጋ ብቻ ለመ/ቤታችን ማቅረብ አለባቸው
9. ተጫራቾች በዝርዝር በተገለጹት የዕቃ ዓይነቶች ባላቸው የፍቃድ አይነት የእቃ አይነቶች በሙሉ ሆነ በከፊል መወዳደር ይጠበቅባቸዋል ፡፡
10. ተጫራቾች የግልጽ ጨረታውን ዋጋ ፀንቶ በሚቆይበት ጊዜ በግልጽ መረዳትና በተግባር ላይ ማዋል አለባቸው።
11. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው የዕቃ ሽያጭ ዋጋ ሁኔታ መ/ቤቱ በጠየቀው እስፔስፍኬሽን መሠረት መሆን አለበት።
12. ተጫራቾች ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑ ግብር የተከፈለበትን የቫት ተመዝጋቢና የምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒውን ከዋናው ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
13. ግልጽ ጨረታው በአየር ላይ ከሚቆይበት ቀናቶች ውጪ ዘግይተው የሚቀርቡ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
14. ግልጽ ጨረታው ጨምሮ በማስታወቂያ ከወጣበት ለ15 ተከታታይ ቀን ቅዳሜና እሁድን በመጨረሻ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጨረታው ተዘግቶ በማስታወቂያ ከወጣበት በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡10 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
15. ግልጽ ጨረታው በተጫራቾች ፊት በግልጽ ይነበባል፣ የግልጽ ጨረታ አከፋፈት ዝርዝር ቃለ ጉባዔ ተይዞ በመ/ቤቱ ጨረታ ኮሚቴ ይፈረማል እንዲሁም በግልጽ ጨረታው አከፋፈቱ ላይ የተገኙ ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በግልጽ ጨረታው አከፋፈት ስነ-ስርዓት ላይ ስለመገኘታቸው እንዲፈራረሙ ይደረጋል፡
16. የአገልሎት ጊዜው መ/ቤት የግልጽ ጨረታውን አሸናፊውን ከለየ በኋላ ለአሸናፊው ድርጅት በጽሁፍ ያሳውቃል
17.የአገልግሎት ጊዜው መ/ቤት የግልጽ ጨረታ አሸናፊውን ለይቶ ካሳወቀ በኋላ በ3 ቀናት ውስጥ በቀረበው ዋጋ መሰረት ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ውል ይገባል ፡፡
18. የግልጽ ጨረታን በሚመለከት ጨረታውን ለማሸነፍ እንዲረዳው ለማንኛውም ኃላፊ እና ሠራተኛ መደለያ የሰጠ ተጫራች ከግልጽ ጨረታው የሚሰረዝ እና አሸንፎም ውል ቢዋዋል ውሉ የሚሰረዝ መሆኑንና በህግ የሚያስቀጣው እንደሆነ ማወቅ ይኖርበታል ፡፡
19. ተጫራቾች የግልጽ ጨረታን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ለእያንዳዱ ሎት ሲፒኦ (CPO) 10,000 /አስር ሺህ/ማስያዝ ይኖርበታል ቢድ ቦንድ ማስያዝ ፈጽሞ አይፈቀድም፡፡
20. በዚህ የግልጽ ተጫራቾች መመሪያ ላይ የተገለጹትን ያልፈጸመ በተራ ቁጥር 19 ላይ የተመለከተውን የጨረታ ማስከበሪያው ሊያስቀጣው ይችላል፡፡
21. ተጫራቾች በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ፖስታ በማያያዝ ግልጽ ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ቤ/ጉ/ክልል አሶሳ ከተማ በሚገኘው በጽ/ቤቱ ግዢና ንብረት ዳሪክቶሬት ቢሮ ቁጥር 104 በመቅረብ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
22. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ግልጽ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
23. ሁሉም ተጫራቾች ግልጽ ጨረታው ከሚከፈትበት ቀን በፊት ሙሉ በሙሉ የግልጽ ጨረታ ሰነዳቸውን ቀድመው ካስገቡ የጨረታ መክፈቻ ጊዜውን ሳይጠብቅ ለተጫራቾች በስልክ ጥሪ ተደርጎ ይከፈታል፡፡
24. ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ አሶሳ ከተማ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና ካብኔ ጉዳዮች ጽ/ ቤት ግዢና ንብረት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 104 ይከፈታል፡፡
አድራሻ ስልክ ቁጥር 09 21 17 78 90/ 057-775-2499/057 775 0142 | 057 775 0031 /09 15 89 09 36
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት