አማራ ብረታ ብረት ኢንዱስትሪ እና ማሽን ቴክኖሎጂ ልማት ኢንተርፕራይዝ የፋውንደሪ ወይም የብረታ ብረት ማቅለጥ ኤክስፐርት/ተቋም በመቅጠር የምርት ጥራትን፣ ደህንነትን እና የምርት ቅልጥፍናን ለማረጋገጥ፣ የሚቀልጡ ማቴሪያሎችን በሚፈለገዉ መንገድ በመቀየጥ የፋውንደሪ ስራዎችን በስራ ላይ ስልጠና እንዲሰጥና እንዲመራ ይፈልጋል


Reporter(Oct 12, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

ማስታወቂያ

አማራ ብረታ ብረት ኢንዱስትሪ እና ማሽን ቴክኖሎጂ ልማት ኢንተርፕራይዝ የፋውንደሪ ወይም የብረታ ብረት ማቅለጥ ኤክስፐርት/ተቋም በመቅጠር የምርት ጥራትን, ደህንነትን እና የምርት ቅልጥፍናን ለማረጋገጥ ፤ የሚቀልጡ ማቴሪያሎችን በሚፈለገዉ መንገድ በመቀየጥ የፋውንደሪ ስራዎችን በስራ ላይ ስልጠና እንዲሰጥና እንዲመራ ይፈልጋል።

የአማራ የብረታ ብረት ኢንዱስትሪና ማሽን ቴክኖሎጅ ልማት ኢንተርፕራይዝ በአምራች ኢንዱስትሪዉና በግብርናዉ ዘርፍ ዉስጥ ያለውን የቴክኖሎጂ ፍላጎት፣ አቅርቦት፣ አጠቃቀምና ውስንነቶችን በመቅረፍ የክልሉን ብሎም የሃገርን ኢንዱስትሪላይዜሽን ሽግግር እዉን ለማድረግ በደንብ ቁጥር 127/2007 ዓ.ም የተቋቋመ የመንግሥት የልማት ድርጅት ነው።

በዚህ መሠረት ከላይ የተመለከተውን ራዕይና ግብ ለማሳካት ያለውን ፋሲሊቲ በመጠቀም (የቅርጽ ማዉጫ ሂደቶችን በመጠቀም ማለትም (NO-Backe & shell molding line) ብረታማ እና ብረት ያልሆኑ ቁሳቁሶችን ለማቅለጥ) ድርጅቱ የፋውንደሪ ወይም የብረታ ብረት ማቅለጥ ኤክስፐርት/ተቋም በመቅጠር የምርት ጥራትን, ደህንነትን እና የምርት ቅልጥፍናን ለማረጋገጥ ፤ የሚቀልጡ ማቴሪያሎችን በሚፈለገዉ መንገድ በመቀየጥ የፋውንደሪ ስራዎችን በስራ ላይ ስልጠና እንዲሰጥና እንዲመራ ይፈልጋል።

በመሆኑም ኢንተርፕራይዙ አብረዉት የሚሰሩ አጋር ግለሰቦችና ድርጅቶችን አወዳድሮ መምረጥ ስለሚፈልግ በEmail address amharametalindustry@gmail.com  ህጋዊ ፈቃድ ወይም ልምድ ያላችሁ ግለሰቦች/ድርጅቶች በኢንተርፕራይዙ ዋናው መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 25 በአካል በመገኘት ወይንም በEmail address amharametalindustry@gmail.com  ፕሮፖዛል ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ እንድታቀርቡ ኢንተርፕራይዙ ይጋብዛል:: ለበለጠ መረጃ የሪፖርተር ጋዜጣ ይመልከቱ።

አድራሻ፡- ባሕር ዳር ቀበሌ 17 ቢሮ ቁጥር 25
ስልክ፡- 0582219986/0991494311
Email address amharametalindustry@gmail.com 
ባህር ዳር፣ኢትዮጵያ
አማራ ብረታ ብረት ኢንዱስትሪና ማሽን ቴክኖሎጂ ልማት ኢንተርፕራይዝ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *