የኮልፌ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የመምህራን እና ሠራተኞች የካፌ አገልግሎት ሥራ ማሠራት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 14, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ 

የጨረታ ቁጥር 002/2018 ዓ.ም

የኮልፌ አጠቃላይ 2 ደረጃ /ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • የመምህራን እና ሠራተኞች የካፌ አገልግሎት ሥራ ማሠራት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ የተጫራቾች መመሪያ

  1. ተጫራቾች ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሕጋዊ ደረሰኝ ያላቸው መሆን አለባቸው።
  2. ተጫራቾች የተጠቀሱትን አገልግሎት የሚሸጡበትን የአንዱን ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ጨምሮ በመግለጽ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውን እና የጨረታ ዓይነት በግልፅ በመጻፍ እንዲሁም ተሞልቶ የዋጋ ዝርዝር ጋር መደበኛ የጨረታ ሰነዱ ሙሉ በሙሉ መመለስ አለበት የጨረታ ሰነዱ ካልተመለሰ የጨረታ ውድድሩ ላይ መቅረብ የማይችሉ መሆኑን እየገለፅን በአግባቡ የተሞላውን የጨረታ ሰነድ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የኮልፌ አጠቃላይ 2 ደረጃ /ቤት የግ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 6 የጨረታ ሳጥን መግባት ይኖርበታል።
  3. ተጫራቾች ሙሉ በሙሉ ስማቸውን፣ አድራሻቸውንና፤ ፊርማቸውን በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ በመፈረም ማቅረብ አለባቸው ሰነዶቹ በማኅተም መረጋገጥ አለባቸው።
  4. በጨረታው አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ድርጅት ከግዥ አስተዳደሩ ጋር በሚገባው ውል መሠረት አገልግሎቱን እንደስፈላጊነቱ ማቅረብ አለበት።
  5. አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል።
  6. ተጫራች የመ/ቤቱ የምግቡን ጥራት ተቆጣጣሪ ኮሚቴ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት አይቶ /ቤቱ ካወጣው የጨረታ ሰነድ እና በጨረታው እንዲያልፍ የማይመጣም ከሆነና ጥራት የጎደለው ነው ብሎ ካመነ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ውሉን ማቋረጥ ይችላል።
  7. በጨረታው ያሸነፈ አካል ማሸነፉ እንደተገለፀለት ከመ/ቤቱ ጋር በ15 ውስጥ ቀርቦ ውል መፈፀም አለበት።
  8. የግዥ ውል በሚፈፀምበት ጊዜ ሰነድ ላይ የተሰጠው የአገልግሎት ብዛት በተወሰነ መጠንን ሊጨምርም ወይም ሊቀንስ የሚችል መሆኑን ተጫራቹ አውቆ የመጫረት ግዴታ አለበት።
  9. የሚሸጠው የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ መክፈል ይኖርበታል።
  10. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ11ኛ ቀን 400 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ተዘግቶ 430 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  11. የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  12. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም /ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  13.  የጥቃቅን እና አነስተኛ ተወዳዳሪዎች ይበረታታሉ።

ለበለጠ መረጃ አድራሻ

  • አዲስ ከተማ ክፍስ ከተማ ወረዳ 11 18 ሉኳንዳ ወደ አሸዋ ሜዳ በሚወስደው መንገድ ይገኛል።
  • ስልክ ቁጥር 0111-2790012-0112738757

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ

የኮልፌ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት 


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *