Your cart is currently empty!
በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ የአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል የአዳሬ ሆስፒታል B+G+8 ህንጻን ሊፍት/ አሳንሰር ሥራ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 14, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ የአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል የአዳሬ ሆስፒታል B+G+8 ህንጻን ሊፍት/አሳንሰር ሥራ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ማህበራት ተጫራቾች መጫረት ይችላሉ፡–
- በኮንስትራክሽን ዘርፍ BC-1/GC-2 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ተቋራጮች
- በሥራ መስክ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፣
- የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲፒኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ለእያንዳንዱ ሎት ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት፣
- የጨረታ ሰነዱ ከአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ግዥና ክፍያ ፋይናንስ ክፍል በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /ለአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 1000/አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል መግዛት ይቻላል፣
- ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴክኒካል አንድ ኦርጅናል፣ 2(ሁለት ኮፒ እና ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናል፣ 2(ሁለት) ኮፒ ሁሉም ላይ ፊርማና የድርጅቱ ማህተም የተደረገበትን በመያዝ አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ግዥና ክፍያ ፋይናንስ ክፍል (ግዥ ኬዝ– ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
- ጨረታው በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት በአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ግዥና ክፍያ ፋይናንስ ክፍል ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ የሚሆን ከሆነ በሚቀጥለው ሰኞ ጨረታው የሚገባበትና የሚከፈትበት ቀን እና ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው ሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፣
- በጨረታ አከፋፈት ስነ–ሥርዓት የተነበበው ዋጋ እና በአርትሜትክ ቼክ በሚደረግበት ጊዜ በሁለቱ መካከል ከ2% በላይ ሆነ በታች ልዩነት ካለ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል፣
- በጨረታው ላይ ባለው ጠቅላላ ዋጋ ከአስር ፐርሰንት(10%) በላይ የዋጋ ቅናሽ (Rebate) የተደረገ ከሆነ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል፣
- ተጫራቹ ከመሀንዲስ ግምት አስራ አምስት ፐርሰንት (5%) በታችና በላይ ያቀረበ ከሆነ ከጨረታ ውጪ ይሆናል፣
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
ለተጨማሪ መረጃ
ስልክ ቁጥር፡– 046-220 82 02/ 046-220-45-66
በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ የአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል