Your cart is currently empty!
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ንብረት የሆኑትን የተለያዩ ተሽከርካሪዎች (ማሽነሪዎችና መኪናዎች) ማለስለሻ ቅባትና ዘይት ግዥን ለመፈጸም እንዲቻል በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 14, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ንብረት የሆኑትን የተለያዩ ተሽከርካሪዎች (ማሽነሪዎችና መኪናዎች) ማለስለሻ ቅባትና ዘይት ግዥን ለመፈጸም እንዲቻል በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድረጅቶች መወዳደር ይችላሉ።
1. በሥራ ዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣
3. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣
3. የዘመኑ የታከስ ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው፣
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲፒኦ (CPO ) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት፡፡
5. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /ለአስር/ ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም ብር 400/ አራት መቶ / በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
6. ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም በፋይ/ኢኮ/ልማ/መምሪያ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
7. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከቀኑ 3:30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት፤ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር፡-046-212-13-34 ደውለው ይጠይቁ።
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ
ሀዋሳ