በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሰሜን ሸዋ ዞን የአንጐለላና ጠራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት የተለያዩ የደን ዘር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 14, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡– 04/2018

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሰሜን ሸዋ ዞን የአንጐለላና ጠራ ወረዳ ገንዘብ /ቤት በመደበኛ በጀት የተለያዩ የደን ዘር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሆነም በጨረታው መካፈል የምትፈልጉ፡

1. ተጫራቾች በዘርፉ በዘመኑ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN No / ያላቸውና ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ ብር በላይ ዋጋ ባላቸው ግዥዎች የሚሳተፉ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ እና ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ፤

2. የደን ዘሩ በአንድ ጊዜ በአይነት፣ በመጠንና በጥራት ሳያጓድል ማቅረብ የሚችሉ፡፡

3. ተጫራቾች በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ አድራሻቸውንና ፊርማቸውን ማስፈር አለባቸው፡፡

4. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ፤ ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሞልተው በመፈረምና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋና እና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም /ዋና /ቤት በመሂ 1 ያስያዙበትን ደረሰኝ ከኦሪጅናል ዋጋ ማቅረቢያ ውስጥ መያያዝ አለበት፡፡ የእቃ ግዥው /ቤቱን፣ የተጫራቾችን ስምና አድራሻ፣ እንዲሁም የግዥውን አይነት በመጥቀስ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16 ቀን 800 ሰዓት ድረስ በጽ/ቤቱ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

6. ጨረታው በዚሁ ዕለት 16ኛው ቀን 800 ሰዓት ይታሸግና በዕለቱ 8:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል ፡፡

7. 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው በመንግሥት የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡

8. /ቤቱ ጨረታውን በሎት ያወዳድራል፡፡

9. ተጫራቾች የእቃውን አይነትም ሆነ መጠን በጨረታው በሙሉ ወይንም በከፊል መሳተፍ ይችላሉ፡፡ ሆኖም አንድ ተጫራች በአንድ ሎት ውስጥ ከተዘረዘሩት አይነቶች መካከል ከፋፍሎ መጫረት ከሎት ማጉደል አይችሉም፡፡

10. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት አን/////ቤት ጫጫ ከተማ ድረስ በየንብረት ክፍሉ ገቢ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡

11. ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊ በሚሆኑበት ጊዜ ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ውል ከመግባቱ በፊት ናሙና ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡

12. በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ላይ ያልተገለፀ በተጫራቾች መመሪያ እና በኦሪጅናል ሰነዱ ላይ በዝርዝር ስለሚገለጽ ዝርዝራቸውን በትኩረት ማየት ይጠበቅባቸዋል፡፡

13. በማንኛውም ግዥ ለእቃዎች ከብር 20,000 /ሃያ ሺህ/ እና ለአገልግሎት ከብር 10,000 /አስር ሺህ/ በላይ ለሚሆኑ ግዥዎች አቅራቢው ከሚፈጸምለት ክፍያ ላይ 3% ቅድመ ግብር ተቀንሶ የሚቀር ይሆናል፡፡

14. ተጫራቾች በሞሉት ዋጋ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ማድረግና በፍሉድ መደለዝ አይፈቀድም፡፡ ምንአልባት ከጠቅላላ ዋጋ ላይ ስህተት ቢፈጠር አንድ ሰረዝ አድርጐ ስለመሰረዙ መፈረም አለበት፡፡

15. /ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

16. /ቤቱ የሚገኘው ከአ/አበባ በስተሰሜን 110 / ርቀት በደብረብርሃን መስመር ላይ ነው፡፡

17. ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡– 011-6-32-01-47 ደውለው ይጠይቁ፡፡

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ገንዘብ ቢሮ በሰሜን ሸዋ ዞን አንጎለላና ጠራ ወረዳ ገንዘብ /ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *