Your cart is currently empty!
በሲዳማ ክልላዊ መንግስት በሀዋሳ ከተማ የአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ለ2018 በጀት ዓመት የሚሆን የህክምና መገልገያ መሣሪያዎች ግዥ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 14, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ክልላዊ መንግስት በሀዋሳ ከተማ የአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ለ2018 በጀት ዓመት የሚሆን ከዚህ በታች የተጠቀሰው ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1. የህክምና መገልገያ መሣሪያዎች ግዥ
ተጫራቾች
- ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው፣
- የዘመኑን የ2017 ዓ/ም ግብር የከፈሉ፣ እንደ አስፈላጊነቱ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- በመስኩ የንግድ ሥራ የተሰማሩ
- የጨረታ ማስከበሪያ በሆስፒታሉ ስም የተሠራ CPO 10,000 (አስር ሺህ ብር) ማስያዝ የሚችሉ፣
- የጨረታ ሰነዱ አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ግዥ ከፍል በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጅናል ሁለት ኮፒ ለየብቻ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በድምሩ 6 ፖስታ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ እንዲያስገቡ ሆኖ በ15ኛው ቀን ከረፋዱ 6፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ይታሸግና ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ይህ ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው በሥራ ቀን ይከፈታል።
ማሳሰቢያ
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ጨረታው ተከፍቶ ውሳኔ ይሰጣል።
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።
- ፋይናንሻል ሠነድ ከሆስፒታሉ የተዘጋጀው ላይ ብቻ ዋጋ መሙላት ይገባል።
- በፋይናንሻል ሠነድ ላይ የዋጋ መሙያን መቀየርም ሆነ ከተጠየቀው ይዘት ውጪ መለኪያ በመቀየር ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ አይቻልም።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0462122370
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሀዋሳ ከተማ አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል