የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የጎፋ ዞን ሣውላ ከተማ ፋ/ጽ/ቤት ለሣውላ ከተማ አስተዳደር ሴክተር መ/ቤቶች ለ2018 በጀት ዓመት ሞተር ሣይክል ተሽከርካሪዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሴኪዩሪት ካሜራ፣ ጽህፈት መሣሪያና ጽዳት ዕቃዎች፣ ህንፃ መሣሪያ /ግንባታ ዕቃዎች/ በግልጽ ጨረታ አወዳድረው ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 14, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ሣውላ 001/2018

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የጎፋ ዞን ሣውላ ከተማ ፋ/ጽ/ቤት ለሣውላ ከተማ አስተዳደር ሴክተር መ/ቤቶች ለ2018 በጀት ዓመት ከዚህ ቀጥሎ በሎት የተከፋፈሉ ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድረው ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1 ሞተር ሣይክል ተሽከርካሪዎች
  • ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
  • ሎት 3 ሴኪዩሪት ካሜራ
  • ሎት 4 ጽህፈት መሣሪያና ጽዳት ዕቃዎች
  • ሎት 5 ህንፃ መሣሪያ /ግንባታ ዕቃዎች/

በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉት መስፈርቶችን ማሟላት ይኖርባችኋል፡፡

1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው

2. የዘመኑን ግብር የከፈለ፣

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ የሆነ

4. የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር /TIN/ ያለው

5. በአቅራቢነት ላይ የተመዘገቡበት የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችል

6. የመልካም የሥራ አፈፃፀም የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሣ/ከ/ፋ/ጽ/ቤት ስም

  • ለሎት 1 /35,000 /ሠላሳ አምስት ሺህ ብር/
  • ለሎት 2 /50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/
  • ለሎት 3 /30,000 /ሰላሳ ሺህ ብር/
  • ለሎት 4 /60,000 /ስልሳ ሺህ ብር/
  • ለሎት 5 /20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ በባንከ የተመሰከረስት /CPO/ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

8. ተጫራቾቾ ከላይ ከ1-7 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ቴክኒካልና ፋይናንሻል በኮፒና ኦርጅናል ለየብቻ በታሸገ ፖስታ ከላይ ኮፒና ኦርጅናል ብሎ በመፃፍ በእናት ፖስታ አሽገው ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በመንግስት የሥራ ሰዓት ማስገባት ይቻላል።

9. ተጫራቾቸ በእያንዳንዱ የመደበኛ የጨረታ ሰነድ ላይ ያለውን መጠይቅ በመሙላትና በመፈረም የድርጅታችሁን ማህተም በሚታይ መልኩ ማድረግ አለባችሁ።

10. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከሣውላ ከተማ ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 ያገኛሉ።

11. የጨረታ አሸናፊው ያሸነፋቸውን ዕቃ በራሱ ወጪ እስከ ሣውላ ከተማ ፋ/ጽ/ቤት ንብረት ከፍል አምጥቶ ማስረከብ አለበት።

12. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የመንግሥት ሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሣጥኑ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ጨረታው ይከፈታል። 16ኛው ቀን ቅዳሜ ወይም ዕሁድ ወይም በዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል ማለት ነው።

ማሳሰቢያ፦ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- የስ.ቁ 09 08 94 00 07 ይደውሉ።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት

የጎፋ ዞን ሣውላ ከተማ ፋ/ጽ/ቤት