Your cart is currently empty!
የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን የሞተር ብስክሌት እንቅስቃሴ መከታተያ እና መቆጣጠሪያ ሲስተም መተግበሪያ /ሶፍትዌር/ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 15, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር፡ አአትማባ/ብግጨ/አገልግሎት/03/2018
የሞተር ብስክሌት እንቅስቃሴ መከታተያ እና መቆጣጠሪያ ሲስተም መተግበሪያ /ሶፍትዌር/ ግዥ ጨረታ
የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን የሞተር ብስክሌት እንቅስቃሴ መከታተያ እና መቆጣጠሪያ ሲስተም መተግበሪያ /ሶፍትዌር/ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች፦
1. የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) የማይመለስ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ዘወትር በስራ ሰዓት ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡30 ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ በባለስልጣኑ መስሪያ ቤት ግዥ ንብረት አስተዳደር እና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 10-01 መውሰድ ይችላሉ።
2. ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ለሚያቀርቡት አገልግሎት በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
3. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (ሲፒኦ) ተመላሽ የሚሆን 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ማስያዝ አለባቸው።
4. የጨረታው አሸናፊ ሆነው የተመረጡት ድርጅቶች የጨረታው ውጤት በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በአስር የስራ ቀናት ውስጥ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ግዥ ንብረት አስተዳደር እና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክተር ዋና ክፍል በመቅረብ ያሸነፉበትን ዋጋ 10% የመልካም ስራ አፈጻጸም በማስያዝ ውል መፈጸም አለባቸው።
5. የጨረታው አሸናፊ ላልሆኑ ድርጅቶች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ የጨረታው አሸናፊ ተለይቶ የአሸናፊነት ደብዳቤ ከተሰጠው በኋላ ባሉት 5 ቀናት ውስጥ ይመለስላቸዋል።
6. ጨረታው ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት ይዘጋል።
7. ጨረታው ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል።
8. ከጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።
9. ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በተመለከተ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡– ሃያ ሁለት መክሊት ህንፃ 10ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 10-01
ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልገዎ በስልክ ቁጥሮች 0116-672–342 ማነጋገር ይችላሉ።
የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን