የውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን የ 2017 በጀት ዓመት ሂሣቡን በተፈቀደላቸው ኦዲተሮች ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 17, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ሀገር አቀፍ ግልፅ የሂሳብ ምርመራ (የኦዲት)

አገልግሎት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ግልፅ፡– 03/2018

የውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን 2017 በጀት ዓመት ሂሣቡን በተፈቀደላቸው ኦዲተሮች ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም እያንዳንዱ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታ ለመወዳደር ይችላል።

1. ኮርፖሬሽናችን ሂሳብ IFRS መሰረት ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል የኦዲተርነት የሙያ ፈቃድ፣ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር /Tax identification Number (TIN) ያለው፤

2. የዘመኑን ግብር ከፍሎ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለውና ማቅረብ የሚችል፣

3. ተጫራቾች ወቅታዊ ብቃታቸውንና ሙያዊ ስነ ምግባራቸው በተመለከተ ከፈቃድ ሰጪው አካል ከዋናው ኦዲት መስሪያ ቤት እና ከኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ወይም ከሂሳብ አዋቂዎችና የግል ኦዲተሮች ማህበር እንዲሁም ከዚህ በፊት ኦዲት ያደረጓቸው የልማት ድርጅቶች የመልካም ስራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት፣

4. የሂሣብ ምርመራው (ኦዲቱ) ዋና /ቤት ባህር ዳር፣ አዲስ አበባ ማስተባበሪያ /ቤት /አዲስ አበባ/ ኮምቦልቻ ማስተባበሪያ /ቤት /ኮምቦልቻ/ ጫጫ ሜጋ ፕሮጀክት /ደብረብርሃን/ ከተማ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ቅጥር ግቢ መሆኑን አውቆ የሚሳተፍ መሆን አለበት፡፡

5. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 20 /ሃያ የሥራ ቀናት/ በጽ/ቤታችን የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ /100.00 /አንድ መቶ ብር/ ከፍለው ከኮርፖሬሽኑ በመግዛት መጫረት ይቻላል፡፡

6. ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋቸውን (ታክሱን ጨምሮ) በጨረታ መመሪያው መሰረት በመሙላት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን የተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO / ወይም Un Conditional Bank Bid Bond/ ማስከበሪያ የሚሆን የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነድ እና የቴክኒክ መወዳደሪያ ሰነድ 2 የተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ በተራ ቁጥር 5 በተገለጸው የስራ ቀናት ውስጥ ቢሮ ቁጥር 25 ወይም ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒክ ሰነድ ጋር ይካተት፣ በተገለጸው አግባብ ሰነዶቹን አዘጋጅቶና አሽጎ ያልቀረበ ተወዳዳሪ ወይም ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡

7. የጨረታ ሳጥኑ 20ኛው /በሃያኛው ቀን/ ከቀኑ 800 ሰዓት ታሽጎ 830 ሰዓት ይከፈታል ዕለቱ የእርፍት ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት 800 ሰዓት ተዘግቶ 830 ሰዓት በኮርፖሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 25 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ጨረታው ይከፈታል፡፡

8. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡ተጨማሪ ማብራሪያ ከአስፈለገ በስልክ ቁጥር 058-222-1479 መደወል ይቻላል።

የውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *